መዝሙር 74:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ጠላቶች በአንተ ላይ የሚሳለቁት እስከ መቼ ነው? ስምህንስ የሚዳፈሩት ያለማቋረጥ ነውን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ ጠላት የሚያሾፈው እስከ መቼ ነው? ባላንጣስ ለዘላለም በስምህ ያላግጣልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል? ስምህን ጠላት ለሁልጊዜ ያቃልላልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኃጥኣንን ቀንዶች ሁሉ እሰብራለሁ። የጻድቃን ቀንዶች ግን ከፍ ከፍ ይላሉ። |
ዐይንህን በትዕቢት አቅንተህ፥ ድምፅህን ከፍ አድርገህ በመጮኽ የተዳፈርከውና የተሳደብከው ማንን ይመስልሃል? የእስራኤልን ቅዱስ አይደለምን?’
ከእነርሱ አንዱ ቀጭን ሐር ለብሶ ከወንዙ በላይ በኩል የቆመውን መልአክ “ይህ ሁሉ አስደናቂ ነገር ፍጻሜ እስከሚያገኝ ምን ያኽል ጊዜ ይወስዳል?” ብሎ ጠየቀው።
እነርሱ በታላቅ ድምፅ “ቅዱስና እውነተኛ፥ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ በምድር ባሉት ሰዎች ላይ የማትፈርደውና ስለ ደማችንም የማትበቀለው እስከ መቼ ነው!” እያሉ ጮኹ።