መዝሙር 73:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቅጽበት ተደመሰሱ፤ መጨረሻቸውም አስደንጋጭ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዴት ፈጥነው በቅጽበት ጠፉ! በድንጋጤ ፈጽመው ወደሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ፥ በድንጋጤ ጠፉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምትገዛልህን ነፍስ ለአራዊት አትስጣት፤ የድሆችህንም ነፍስ ለዘወትር አትርሳ። |
ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ሰው ይህ መጥፎ ዕድል መቼ እንደሚገጥመው አያውቅም፤ ወፍ በራ በወጥመድ ውስጥ እንደምትገባ፥ ዓሣም በመጥፎ አጋጣሚ በመረብ እንደሚያዝ እንዲሁም የሰው ልጅ ሁሉ ሳያስበው ድንገት በሚደርስበት በክፉ አጋጣሚ ይጠመዳል።
ስለዚህ ይህ በደላችሁ ተሰነጣጥቆ በማኰፍኰፍ ሊወድቅ እንደ ተቃረበና አወዳደቁም በፍጥነትና በቅጽበት እንደሚደርስበት እንደ ረጅም የቅጽር ግንብ ያደርጋችኋል።
በመተትሽ ልታስወግጂ የማትችይው ክፉ ነገር ይመጣብሻል፤ ልትከላከዪ የማትችይው ችግር ይደርስብሻል፤ ምንም ያላሰብሽው ጥፋት በድንገት ያጋጥምሻል።
እርሱም ራሱ እግዚአብሔር አስቀድሞ ባቀደውና ባወቀው አሠራር መሠረት ለእናንተ ተላልፎ ተሰጠ፤ እናንተም በዐመፀኞች እጅ እንዲሰቀልና እንዲሞት አደረጋችሁት።
ሰዎች “ሁሉ ነገር ሰላምና የተረጋጋ ነው” ሲሉ እርጉዝ ሴትን ምጥ እንደሚይዛት ዐይነት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ በምንም ዐይነት አያመልጡም።
ሥቃይዋንም በመፍራት በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ፥ አንቺ ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን ሆይ! ፍርድሽ በአንድ ሰዓት ውስጥ ስለ መጣ፥ ወዮልሽ! ወዮልሽ!” ይላሉ።
ሳኦልም ሳሙኤል በተናገረው ቃል ደንግጦ በመዝለፍለፍ ወደቀ፤ በመሬት ላይም ተዘረረ፤ ቀኑንና ሌሊቱን ሁሉ እህል ስላልቀመሰ ድካም ተሰምቶት ነበር።