መዝሙር 68:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደጋግ ሰዎች ግን ደስ ይበላቸው፤ በፊቱም ሐሴት ያድርጉ፤ በደስታም ይፈንጥዙ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፤ በእግዚአብሔር ፊት ሐሤት ያድርጉ፤ ደስታንና ፍሥሓን የተሞሉ ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ፥ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ ክፉዎች ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጩኸት ደከምሁ፥ ጉሮሮዬም ሻከረ፤ አምላኬን ተስፋ ሳደርግ ዐይኖቼ ፈዘዙ። |
አምላክ ሆይ! ከዚያም በኋላ ለአንተ ለምታስደስተኝ ወደ መሠዊያህ ሄጄ እሰግድልሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ በገናዬን እየደረደርኩ አመሰግንሃለሁ።
እናንተ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻችሁ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻችሁ፥ እንዲሁም ከእናንተ ጋር የርስት ክፍያ ከሌላቸው በከተሞቻችሁ ከሚኖሩ ከሌዋውያን ጋር በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ትደሰታላችሁ።
ኢየሱስ ክርስቶስን ያላያችሁት እንኳ ብትሆኑ ትወዱታላችሁ፤ አሁን እንኳ የማታዩት ብትሆኑ ታምኑበታላችሁ፤ በቃላት ሊገለጥ በማይቻልና በከበረ ደስታ ደስ ይላችኋል።
ሰማይ ሆይ! በእርስዋ ደስ ይበልህ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ በእርስዋ ላይ ስለ ፈረደባት እናንተ ቅዱሳንና ሐዋርያት ነቢያትም ደስ ይበላችሁ!