መዝሙር 58:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሾኽ በእሳት ላይ ተደርጎ ከመሞቁ በፊት ፈጥነህ ጠራርገህ አጥፋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእሾኽ እሳት ገና ድስታችሁን ሳያሰማው፣ ርጥቡንም ደረቁንም እኩል በዐውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደሚሟሟ ቀንድ አውጣ፥ ፀሐይን እንዳላየ ጭንጋፍ ይሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀይሌን ወደ አንተ አስጠጋለሁ፥ አንተ አምላኬና መጠጊያዬ ነህና። |
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።
ሕዝቦች እንደ ኀይለኛ ውሃ ድምፅ ያሰማሉ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲገሥጻቸው በተራራ ላይ ገለባዎች በነፋስ እንደሚበተኑና በዐውሎ ነፋስም ዐቧራ እንደሚበተን ርቀው ይሸሻሉ።
እነርሱ ገና እንደ በቀለና ሥር እንዳልሰደደ አዲስ ተክል ናቸው፤ እግዚአብሔር ነፋሱን ሲልክ ወዲያውኑ ይደርቃሉ፤ እንደ ገለባም በነው ይጠፋሉ።
ነገር ግን እግዚአብሔር ተሰምቶ የማይታወቅ አዲስ ነገር በመፍጠር በሕይወታቸው ሳሉ ወደ ሙታን ዓለም ይወርዱ ዘንድ ምድር ተከፍታ እነርሱንና የእነርሱ የሆነውን ሁሉ ብትውጥ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን የተቃወሙ መሆናቸውን ታውቃላችሁ።”