መዝሙር 52:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከደግነት ይልቅ ክፋትን፥ ከእውነት ይልቅ ሐሰትን ትመርጣለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከበጎ ነገር ይልቅ ክፋትን፣ ጽድቅን ከመናገር ይልቅ ዐመፃን ወደድህ። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃያል ሆይ፥ በክፋት ለምን ትኩራራለህ? ሁልጊዜስ በመተላለፍ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉ ተካክሎ በአንድነት በደለ፤ አንድ ስንኳ በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እኔን የማያውቁ ሞኞች ሆነዋል፤ ማስተዋል ስለ ጐደላቸው እንደ ሕፃናት የሚታለሉ ናቸው፤ ክፉ ነገር ለመሥራት የተራቀቁ ብልኆች ናቸው፤ መልካም ነገር ማድረግ ግን ከቶ አይሆንላቸውም።”
አንደበታቸው ዘወትር ተንኰል ስለሚናገር፥ እንደ አደገኛ ፍላጻ ነው፤ እያንዳንዱ ባልንጀራውን በፍቅር ቃል ያነጋግረዋል፤ ነገር ግን በስውር ወጥመድ ይዘረጋበታል።
እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ልጆች ናችሁ፤ ፍላጎታችሁም የአባታችሁን ምኞት መፈጸም ነው፤ እርሱ ከመጀመሪያ አንሥቶ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነት በእርሱ ስለሌለ ከእውነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ እርሱ ሐሰተኛና የሐሰት ሁሉ አባት ስለ ሆነ ሐሰት በሚናገርበት ጊዜ ከገዛ ራሱ አውጥቶ ይናገራል።
ይህም የሆነው የእግዚአብሔርን እውነት በሐሰት ስለ ለወጡ፥ በፈጣሪ ፈንታ ፍጡርን ስላመለኩና ስለ አገለገሉ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ለዘለዓለም የተመሰገነ ነው፤ አሜን።
እንደ ውሻ የሚልከፈከፉ፥ አስማተኞች፥ አመንዝሮች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸትን የሚወዱና በሐሰት መንገድ የሚሄዱ ሁሉ ከከተማይቱ ውጪ ይሆናሉ።