“እግዚአብሔር የሰማይ አምላክ ሆይ! አንተ ታላቅ ነህ፤ እኛም በፍርሃት በፊትህ እንቆማለን፤ አንተ ከሚወዱህና ትእዛዞችህንም ከሚጠብቁ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳንህን ትጠብቃለህ።
መዝሙር 47:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድር ሁሉ ላይ ታላቁ ገዢ ልዑል እግዚአብሔር ምንኛ አስፈሪ ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድር ሁሉ ላይ ታላቅ የሆነው ንጉሥ፣ ልዑል እግዚአብሔር የሚያስፈራ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለምድር ሁሉ ደስታን የሚያዝዝ፥ የጽዮን ተራራዎች በመስዕ በኩል ናቸው። የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናት። |
“እግዚአብሔር የሰማይ አምላክ ሆይ! አንተ ታላቅ ነህ፤ እኛም በፍርሃት በፊትህ እንቆማለን፤ አንተ ከሚወዱህና ትእዛዞችህንም ከሚጠብቁ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳንህን ትጠብቃለህ።
ጸሎታችንን ሰምተህ ድልን ታጐናጽፈናለህ፤ እኛንም ለማዳን ብዙ ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህ፤ ሩቅ ከሆነው ባሕር ማዶ ያሉት ሳይቀሩ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ይታመናሉ።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከመቅደሱ በሚገለጥበት ጊዜ እጅግ ያስፈራል፤ እርሱ ለሕዝቡ ብርታትንና ኀይልን ይሰጣል። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ የተከበረስለሆነ፥ ከበግ መንጋዎቹ መካከል አውራ በግ እያለው ለተሳለው ስለት ነውር ያለበትን በግ መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ የተረገመ ነው!” ይላል የሠራዊት አምላክ።
“በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግ ቃላት በጥንቃቄ ባትፈጽሙ፥ አስደናቂና አስፈሪ የሆነውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ባታከብሩ፥