መዝሙር 39:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኃጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤ ሞኞች እንዲሳለቁብኝ አታድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኀጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤ የሞኞች መሣለቂያ አታድርገኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ አሁንስ ማንን እጠብቃለሁ? ተስፋዬ በአንተ ነው።። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።” |
እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ካህናት፥ በመሠዊያውና በመተላለፊያው መካከል ሆነው ያልቅሱ፤ “ጌታ ሆይ! ለሕዝብህ ራራ፤ አሕዛብ አምላካችሁ የት አለ? በማለት እንዲንቁንና እንዲዘባበቱብን አታድርግ” ይበሉ።
ስለዚህም እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ እህል፥ የወይን ጠጅና የወይራ ዘይት እስክትጠግቡ ድረስ እሰጣችኋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ አሕዛብ መዘባበቻ እንዲያደርጉአችሁ አልፈቅድም።
ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።