Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 25:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ስምህ ክብር እጅግ የበዛውን ኃጢአቴን ይቅር በልልኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአቴ ታላቅ ነውና፣ ስለ ስምህ ይቅር በልልኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 አቤቱ፥ በደሌ ብዙ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እኔ ግን በየ​ዋ​ህ​ነቴ እኖ​ራ​ለሁ፤ አቤቱ፦ አድ​ነኝ ይቅ​ርም በለኝ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 25:11
14 Referencias Cruzadas  

አዳኛችን አምላክ ሆይ! እርዳን፤ ስለ ራስህ ክብር ስትል ተቤዠን፤ ኃጢአታችንንም ይቅር በልልን።


ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአታችሁ በኢየሱስ ስም ይቅር ስለ ተባለላችሁ እጽፍላችኋለሁ።


አንተ መጠጊያ ምሽጌ ነህ፤ ስለ ስምህ ስትል ምራኝ፤ የምሄድበትንም መንገድ አሳየኝ።


ይህም ሁሉ ሆኖ ኃጢአታችሁን ይቅር የምል አምላክ እኔ ነኝ፤ ይህንንም የማደርገው ስለ እናንተ ሳይሆን ስለ እኔነቴ ነው፤ ስለዚህ ኃጢአታችሁን አልቈጥርባችሁም።


ነገር ግን የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታው እንደ ሰው ኃጢአት አይደለም፤ በአንድ ሰው ኃጢአት ምክንያት ብዙዎች እንደ ሞቱ እንዲሁም በእግዚአብሔር ጸጋና በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት የተገኘው የጸጋ ስጦታ ለብዙዎች ተትረፍርፎ ተሰጥቶአል።


“እንግዲህ እነሆ፥ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምልህን ሁሉ ንገራቸው፤ ከእንግዲህ ወዲህ የማደርግላችሁ ነገር በሄዳችሁበት ስፍራ ሁሉ ስላሰደባችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ እንጂ ስለ እናንተ ስለ እስራኤላውያን ብዬ አይደለም።


ነገር ግን አብረዋቸው በሚኖሩት ሕዝቦች ፊት ከግብጽ እንደማወጣቸው ለእስራኤላውያን ቃል ገብቼ ነበር፤ ስለዚህ ስሜ እንዳይነቀፍ እነርሱን ከግብጽ እንዲወጡ አድርጌአለሁ።


“ስለ ስሜ ክብር ቊጣዬን አዘገያለሁ፤ ሰዎችም ያመሰግኑኝ ዘንድ ቊጣዬ እንዳያጠፋችሁ እገታዋለሁ።


ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ለክብርህ ተገቢ የሆነውን አድርግልኝ፤ ዘለዓለማዊው ፍቅርህም ድንቅ ስለ ሆነ አድነኝ።


እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ክብርህ ሕይወቴን ጠብቅ፤ በእውነተኛነትህም ከችግሬ ሁሉ ነጻ አውጣኝ።


ዘለዓለማዊ ፍቅሬንም እስከ ብዙ ሺህ ትውልድ እጠብቃለሁ፤ በደልን መተላለፍንና ኃጢአትን ሁሉ ይቅር እላለሁ፤ ነገር ግን እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ ስለ ወላጆቻቸው ኃጢአት ከመቅጣት አልገታም።”


ሕዝቤም ወደ እኔ እንዲህ በማለት ይጮኻሉ፤ ‘ምንም እንኳ የበደላችን ብዛት በእኛ ላይ ቢመሰክርም፥ እግዚአብሔር ሆይ! በተስፋ ቃልህ መሠረት እርዳን፤ ከአንተ ርቀናል፤ አንተንም አሳዝነናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios