Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 35:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ይኸዋ! ይኸዋ! እኛ ራሳችን የሠራኸውን አየን!” እያሉ በመጮኽ ያሳጡኛል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 አፋቸውን አስፍተው ከፈቱብኝ፤ “ዕሠይ! ዕሠይ! በዐይናችን አየነው” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አፋቸውንም በእኔ ላይ አላቀቁ፥ እሰይ እሰይ፥ ዓይናችን አየው ይላሉ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 35:21
11 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ኀይሌን አድክሞ ስላዋረደኝ፥ እነርሱ ልጓሙ እንደ ወለቀለት ፈረስ እንዳሻቸው ፈነጩብኝ።


የሚበላውን ነገር አድኖ ለመቦጫጨቅ እንደሚያገሣ አንበሳ ጠላቶቼ አፋቸውን ከፈቱብኝ።


ጒልበቴ ደክሞ እንደ ውሃ ፈሰሰ፤ አጥንቶቼ ሁሉ ከመገጣጠሚያቸው ተለያዩ፤ ልቤም እንደ ሰም በውስጤ ቀለጠ።


በእኔ ውድቀት “እሰይ! እሰይ!” የሚሉ በኀፍረት ይሸማቀቁ።


አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ግን ደስ ይበላቸው፥ ሐሴትም ያድርጉ፤ ያንተን ማዳን የሚወዱ ዘወትር፦ “እግዚአብሔር ታላቅ ነው!” ይበሉ።


ከችግሬ ሁሉ አድነኸኛል፤ የጠላቶቼንም ውድቀት አየሁ።


እሰይ! እሰይ! እያሉ የሚያፌዙብኝ ሁሉ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።


እርሱ ከምሥራቅ ሶርያውያንን፥ ከምዕራብ ፍልስጥኤማውያንን ልኮ እስራኤልን እንዲወሩ አደረገ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ቊጣው አልበረደም፤ ስለዚህ እጁ እነርሱን ለመቅጣት እንደ ተቃጣ ነው።


ጠላቶቻችሁ ሁሉ በእናንተ ላይ አፋቸውን ይከፍታሉ፤ ያሽሟጥጣሉ ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፤ እንዲህ ሲሉም ይጮኻሉ፦ “ደመሰስናቸው! እሰይ ይህ የምንመኘው ቀን ነበር! በመጨረሻም አየነው።”


ለአሞናውያን፥ ጌታ እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ በላቸው፦ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቤተ መቅደሴ እንዲረክስ በተደረገ ጊዜ፥ የእስራኤል ምድር ባድማ በሆነ ጊዜ፥ የይሁዳ ሕዝብ ተማርኮ በተወሰደ ጊዜ እሰይ ብላችኋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos