Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 35:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ይህን ተመልክተሃል፤ ስለዚህ ጌታ ሆይ! ዝም አትበል! ከእኔም አትራቅ!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን አይተሃልና ዝም አትበል፤ ጌታ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 አቤቱ፥ አንተ አየኸው፥ ዝም አትበል፥ አቤቱ፥ ከእኔ አትራቅ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 35:22
14 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ! ስለምን እንደዚህ ርቀህ ትቆማለህ? በችግር ጊዜስ ስለምን ትሰወራለህ?


ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን ጭንቀት አይቻለሁ፤ በአስጨናቂዎቻቸው ምክንያት የሚጮኹትን ጩኸት ሰምቼአለሁ፤ ጭንቀታቸውንም ዐውቃለሁ።


መከታዬ እግዚአብሔር ሆይ! ወደ አንተ ስጣራ ጩኸቴን ስማ! አንተ ካልሰማኸኝ ግን ወደ መቃብር ከሚወርዱት እንደ አንዱ መሆኔ ነው።


አምላክ ሆይ! ከእኔ አትራቅ፤ አምላክ ሆይ! ፈጥነህ እርዳኝ።


እግዚአብሔር ሆይ! አትተወኝ፤ አምላኬ ሆይ! ከእኔ አትራቅ።


መከራ ሊደርስብኝ ስለ ተቃረበና የሚረዳኝም ስለሌለ እባክህ ከእኔ አትራቅ!


“እነሆ፥ በፊቴ ተመዝግቦአል፤ በእርግጥ በሙሉ እከፍላቸዋለሁ እንጂ ዝም አልልም።”


አምላክ ሆይ! እባክህ ዝም አትበል፤ አትተወን፤ ችላ አትበል!


ይህን ስታደርግ ዝም በማለቴ እኔም እንደ አንተ የሆንኩ መሰለህን? አሁን ግን ፊት ለፊት ነገሩን ገልጬ እገሥጽሃለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ ሳለቅስም ቶሎ ብለህ እርዳኝ፤ እኔ ለጥቂት ጊዜ የአንተ እንግዳ ነኝ፤ እንደ ቀድሞ አባቶቼም በስደተኛነት የምኖር ነኝ።


እግዚአብሔር ሆይ! ከእኔ አትራቅ፤ ረዳቴ ሆይ! እኔን ለመርዳት ፈጥነህ ድረስ።


በግብጽ ያለውን የሕዝቤን ጽኑ መከራ በእርግጥ አይቼአለሁ፤ የጭንቀት ጩኸታቸውንም ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ላድናቸው ወርጃለሁ፤ አሁንም ና! እኔ አንተን ወደ ግብጽ እልክሃለሁ።’


አምላክ ሆይ! አንተ ግን ችግርንና ጭንቀትን አይተህ ልታስወግዳቸው መፍትሔ ታዘጋጃለህ፤ ችግረኛ ራሱን ለአንተ ይሰጣል፤ አንተም የሙት ልጆችን ትረዳለህ።


ብዙ ጠላቶች እንደሚዋጉ በሬዎች ከበውኛል፤ እንደ ባሳን ተዋጊ ኰርማዎችም በዙሪያዬ ናቸው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios