መዝሙር 37:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ አድራጊዎች ይገደላሉ፤ በእግዚአብሔር የሚታመኑ ግን ምድርን ይወርሳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሰዎች ይጠፋሉና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ምድርን ይወርሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና፥ በጌታ ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ፈቃዴ ሁሉ በፊትህ ነው፥ ጩኸቴም ከአንተ አይሰወርም። |
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።
ርዳታ ለማግኘት በምትጮኹበት ጊዜ እስቲ የሰበሰባችኋቸው ጣዖቶቻችሁ ያድኑአችሁ! እነርሱን የነፋስ ሽውታ ያስወግዳቸዋል፤ እስትንፋስም ይወስዳቸዋል፤ በእኔ የሚተማመን ግን ምድሪቱ የእርሱ ትሆናለች፤ የተቀደሰ ተራራዬንም ርስት ያደርጋል።”
በእኔ በእግዚአብሔር ደስ ይላችኋል፤ በምድርም ላይ ከፍ ባለ ቦታ እንድትኖሩ አደርጋለሁ፤ ለቀድሞ አባታችሁ ለያዕቆብ ካወረስኩት ርስት በሚገኘው ምርት እንድትጠግቡ አደርጋችኋለሁ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።
ይህም የሆነው “ሁሉም በምድረ በዳ ይሞታሉ!” ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮ ስለ ነበር ነው፤ ስለዚህም ከየፉኔ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ሁሉም ሞተዋል።
አሁን ግን የሚበልጠውን፥ በሰማይ ያለውን አገር ይናፍቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማን ስላዘጋጀላቸው “አምላካችን” ብለው ቢጠሩት አያሳፍረውም።
ሙሴ፦ ‘አምላኬን እግዚአብሔርን በሙሉ ልብህ ስለ ተከተልከው የረገጥከው ምድር ለአንተና ለልጆችህ የዘለዓለም ርስት ይሆናል’ ” ብሎ በዚያን ቀን በመሐላ ቃል ገብቶልኝ ነበር።