Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 37:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ቊጣ ወደ ክፉ ነገር ስለሚያመራ። ራስህን ከቊጣ መልስ፤ ከንዴትም ተጠበቅ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከንዴት ተቈጠብ፤ ቍጣንም ተወው፤ ወደ እኵይ ተግባር እንዳይመራህ አትከፋ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከቁጣ ራቅ መዓትንም ተው፥ እንዳትበድል አትቅና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ታመ​ምሁ እጅ​ግም ተሠ​ቃ​የሁ፥ ከል​ቤም ኀዘን የተ​ነሣ እጮ​ኻ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 37:8
18 Referencias Cruzadas  

ትዕግሥተኛ ብትሆን አስተዋይ መሆንህን ትገልጣለህ፤ ቊጡ ብትሆን ግን ስንፍናህን ታሳያለህ።


ኀይለኛ ከመሆን ይልቅ ታጋሽ መሆን ይሻላል፤ ብዙ ከተሞችን በጦርነት ድል ነሥቶ ከመያዝ ይልቅ ራስን መቈጣጠር ይበልጣል።


መራራነት፥ ንዴት፥ ቊጣ፥ ሁከት፥ ስድብና ማናቸውም ዐይነት ክፋት ሁሉ ከእናንተ ወዲያ ይራቅ።


ተቈጡ! በቊጣችሁ ግን ኃጢአት አትሥሩ፤ ቊጣችሁም ሳይወገድ ፀሐይ አይጥለቅባችሁ።


አሁን ግን ቊጣን፥ ንዴትን፥ ተንኰልን፥ ስም ማጥፋትን ከእናንተ አስወግዱ፤ የሚያሳፍር ንግግርም ከአፋችሁ አይውጣ።


ቊጣ ሞኝን ይገድለዋል፤ ቅናትም ሰውን ያጠፋል።


ዮናስ በዚህ ነገር ስላልተደሰተ ተበሳጨ፤


እግዚአብሔርም “ስለዚህች ቅል ልትበሳጭ ይገባሃልን?” አለው። ዮናስም “በእርግጥ መበሳጨት ይገባኛል፤ እንዲያውም በንዴት እስከምሞት ድረስ መበሳጨት አለብኝ!” አለ።


አንተ ብትቈጣ ራስህን ትጐዳለህ እንጂ በአንተ ቊጣ ምድር ባዶ አትሆንም። አለቶችም ከስፍራቸው አይነቃነቁም።


እነርሱ እንደሚናገሩት ለመናገር ባስብ ኖሮ ለሕዝብህ ታማኝ ባልሆንኩም ነበር፤


ከድንጋጤዬ የተነሣ ከፊትህ ያራቅኸኝ መስሎኝ ነበር፤ ነገር ግን ርዳታህን ፈልጌ ለምሕረት ወደ አንተ ስጣራ ጩኸቴን ሰማህ።


በፍርሃቴ ጊዜ እንኳ “ማንም የሚታመን የለም” አልኩ።


ንጉሡም “ስለምን ትሄዳለህ? ወደ አገርህ ለመሄድ ያሰብከው ከቶ ምን ተጓድሎብህ ነው?” አለው። ሀዳድም “ምንም የተጓደለብኝ ነገር የለም፤ ብቻ ወደ ትውልድ አገሬ እንድመለስ ፍቀድልኝ” ሲል ለንጉሡ መለሰ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios