መዝሙር 28:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መከታዬ እግዚአብሔር ሆይ! ወደ አንተ ስጣራ ጩኸቴን ስማ! አንተ ካልሰማኸኝ ግን ወደ መቃብር ከሚወርዱት እንደ አንዱ መሆኔ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ዐለቴ ሆይ፤ ሰምተህ እንዳልሰማ አትሁንብኝ፤ አንተ ዝም ካልኸኝ፤ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱ እሆናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ ወደ አንተ እጠራለሁ፥ ዝም ብትለኝ ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልመስል፥ አንተ ዓለቴ ሆይ፥ ዝም አትበለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማልክት ልጆች ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አምጡ፥ የጊደሮችን ጥጃ ለእግዚአብሔር አምጡ። ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ፥ |
እግዚአብሔር ሆይ! መንፈሴ ስለ ዛለብኝ ፈጥነህ መልስ ስጠኝ! ፊትህን ከእኔ አትሰውርብኝ! አለበለዚያ ወደ ጥልቁ ጒድጓድ እንደሚወርዱት ሰዎች እሆናለሁ።
እኔ ወደ መቃብር ብወርድ ምን ይጠቅምሃል? ወደ ዐፈርነት ከተለወጥሁ በኋላ እንዴት ላመሰግንህ እችላለሁ? ታማኝነትህንስ እንዴት መናገር ይቻለኛል?
እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ ሳለቅስም ቶሎ ብለህ እርዳኝ፤ እኔ ለጥቂት ጊዜ የአንተ እንግዳ ነኝ፤ እንደ ቀድሞ አባቶቼም በስደተኛነት የምኖር ነኝ።
ከሙታን ዓለም ሊያመሰግንህ የሚችል አንድ እንኳ የለም፤ ሙታንም ሊያመሰግኑህ አይችሉም፤ ወደ መቃብር የወረዱትም ታማኝነትህን ተስፋ አያደርጉም።
ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ሕዝቦችን እንዳያስት መልአኩ ዘንዶውን ወደ ጥልቁ ጒድጓድ ጣለው፤ ዘግቶም በማኅተም አሸገው፤ ከዚያ በኋላ ለጥቂት ጊዜ መፈታት ይገባዋል።