መዝሙር 25:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንተ የሚታመኑት ኀፍረት አይደርስባቸውም፤ ኀፍረት የሚደርስባቸው፥ በአንተ ላይ ለማመፅ የሚጣደፉት ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣ ከቶ አያፍሩም፤ ነገር ግን እንዲያው ያለ ምክንያት፣ ተንኰለኞች የሆኑ ያፍራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም፥ በከንቱ የሚከዱ ያፍራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምሕረትህ በዐይኔ ፊት ነው፥ በማዳንህም ደስ አለኝ፤ |
ሳኦል ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ ባለመገኘቱ ምክንያት ሞተ፤ እርሱ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አልፈጸመም፤ እንዲያውም የሙታን መናፍስት ጠሪዎችን በመጠየቅ መመሪያ ለማግኘት ሞከረ እንጂ እግዚአብሔርን አልጠየቀም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ገደለው፤ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አስተላለፈ።
እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! አገልጋዮችና ገረዶች የአሳዳሪዎቻቸውን እጅ እንደሚጠባበቁ ሁሉ እኛም እስክትምረን ድረስ የአንተን ምሕረት ለማግኘት እንጠባበቃለን።
በእኔ መከራ ተደስተው ትኲር ብለው በንቀት የሚመለከቱኝ ሁሉ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤ በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ሁሉ ኀፍረትንና ውርደትን ይልበሱ።
የእስራኤል አምላክ ሆይ! አንተን ተስፋ የሚያደርጉ በእኔ ምክንያት አይፈሩ፤ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! አንተን የሚፈልጉ በእኔ ምክንያት አይዋረዱ።
ይህም በሚፈጸምበት ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “እነሆ፥ እርሱ አምላካችን ነው፤ በእርሱ ስለ ታመንን አድኖናል፤ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ እኛም በእርሱ ታምነናል፤ እርሱ ስለ ታደገን በደስታ ተሞልተን ሐሴት እናደርጋለን!” ይላሉ።
ነገሥታት አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል። የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቂአለሽ፤ የእኔን ርዳታ ለማግኘት የሚጠባበቁ ከቶ አያፍሩም።”
እግዚአብሔር ግን እንደ ጀግና ወታደር ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ በመደናቀፍ ኀይል አጥተው ይወድቃሉ። በሚወድቁበትም ጊዜ ክፉኛ ይዋረዳሉ፤ ውርደታቸውም ለረጅም ጊዜ ይታወሳል።