Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 25:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 አምላክ ሆይ! ዱካህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ መንገድህንም አስተምረኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔር ሆይ፤ አካሄድህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ መንገድህንም አስተምረኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፈለግህንም አስተምረኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በከ​ንቱ ሸንጎ አል​ተ​ቀ​መ​ጥ​ሁም፥ ከዐ​መ​ፀ​ኞ​ችም ጋር አል​ገ​ባ​ሁም።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 25:4
11 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ! የእውነት መንገድህን እከተል ዘንድ አስተምረኝ፤ ባልተከፋፈለ ልብም እንዳከብርህ አድርገኝ።


እግዚአብሔር ሆይ! የምመራበትን መንገድ አስተምረኝ፤ በጠላቶቼም ምክንያት በተደላደለ መንገድ ምራኝ።


የምተማመነው በአንተ ስለ ሆነ በየጠዋቱ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ ሕይወቴን በዐደራ ለአንተ ስለ ሰጠሁ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።


እግዚአብሔር ሆይ! የሚጠባበቁኝ ጠላቶቼ ብዙዎች ናቸው! ስለዚህ ፈቃድህን እንዳደርግ ምራኝ፤ መንገድህንም በፊቴ አቅናልኝ።


አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ ዐውቅ ዘንድ እንዳገለግልህና አንተን በማስደሰት እንድቀጥል እባክህ መንገድህን አሳየኝ፤ ይህም ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ተመልከት።”


ሕግህን እንዳስተውል እርዳኝ፤ እኔም ድንቅ ሥራህን አሰላስላለሁ።


እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “በየጐዳናው ቆማችሁ ተመልከቱ፤ ጥንታዊና መልካም የሆነችው መንገድ የትኛዋ እንደ ሆነች ጠይቃችሁ ተረዱ፤ ባገኛችኋትም ጊዜ በእርስዋ ሂዱ፤ በሰላምም ትኖራላችሁ።” ሕዝቡ ግን “በእርስዋ አንሄድም!” አሉ።


ስለዚህ ብዙ ሕዝቦች እንዲህ ይላሉ፦ “ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ስለሚገኝ ኑ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤተ መቅደስም እንሂድ፤ እርሱ ፈቃዱን እንድናደርግ ያስተምረናል፤ እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን።”


የእኔ መንገድ የጽድቅ መንገድ ነው፤ እኔ የምከተለው የፍትሕን ፈለግ ነው።


እግዚአብሔር ሆይ! ቃሌን አድምጥ፤ መቃተቴንም ስማ።


አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ የአገልጋዮችህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ቅን የሆነውንም ነገር ማድረግ ይችሉ ዘንድ አስተምራቸው፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሆይ፥ ለዘለዓለም ርስት አድርገህ ለሕዝብህ በሰጠሃቸው በዚህች ምድር ዝናብ እንዲዘንብ አድርግ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios