መዝሙር 23:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጠላቶቼ ፊት ታላቅ ማእድ አዘጋጀህልኝ፤ ራሴን በዘይት ትቀባልኛለህ፤ ጽዋዬም እስኪትረፈረፍ ድረስ ይሞላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶቼ እያዩ፣ በፊቴ ማእድ አዘጋጀህልኝ፤ ራሴን በዘይት ቀባህ፤ ጽዋዬም ሞልቶ ይፈስሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬንም እስከ አፉ ሞላህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ይቀበላል፥ ምሕረቱም ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። |
አንተ መልካሙን ነገር ትወዳለህ፤ ክፉውን ነገር ትጠላለህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ መረጠህ፤ ከሌሎች ነገሥታትም ይበልጥ የደስታን ዘይት ቀባህ።
የሠራዊት አምላክ በዚህች በጽዮን ተራራ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤ በግብዣውም ላይ ምርጥ የወይን ጠጅና፥ የተሟላ ምግብ ይዘጋጃል።
የወይን ጠጁን በብርሌ ሳይሆን በገምቦ ትጠጣላችሁ፤ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ሽቶ ትቀባላችሁ፤ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ስለ ደረሰው ጥፋት ግን ፈጽሞ አታዝኑም፤ ይህን ሁሉ ስለምታደርጉ ወዮላችሁ!
እኛ እግዚአብሔርን አመስግነን የምንካፈለው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቈርሰው ኅብስት ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?
ከክርስቶስ የተቀበላችሁት መንፈስ በውስጣችሁ ስለሚኖር ሌላ አስተማሪ አያስፈልጋችሁም፤ እርሱ ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ የሚያስተምራችሁም እውነትን ነው እንጂ ሐሰትን አይደለም። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንዳስተማራችሁ በክርስቶስ ኑሩ።