Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 22:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ጌታ ሆይ! የተትረፈረፈ ሀብት ያላቸው ሁሉ ይሰግዱልሃል። ለሞትና ለመቃብር የተቃረቡትም መጥተው ይንበረከኩልሃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 የምድር ከበርቴዎች ይበላሉ፤ ይሰግዱለታልም፤ ነፍሱን በሕይወት ማቈየት የማይችለው፣ ወደ ዐፈር ተመላሽ የሆነው ሁሉ በፊቱ ይንበረከካል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 መንግሥት ለጌታ ነውና፥ እርሱም አሕዛብን ይገዛል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 22:29
20 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ለኢየሱስ ስም ክብር፥ በሰማይና በምድር፥ ከምድር በታችም ያሉት ሁሉ በጒልበታቸው ይንበረከካሉ።


የጢሮስ ሰዎች ስጦታ ያመጡልሻል፤ ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል።


ሙታንህ ተነሥተው ሕያዋን ይሆናሉ፤ እናንተ በመቃብር ውስጥ የምትኖሩ፥ ተነሥታችሁ የደስታ መዝሙር ዘምሩ! አንጸባራቂው ጠል ምድርን እንደሚያድስ እግዚአብሔርም ከሞቱ ብዙ ጊዜ የሆናቸውን ተነሥተው በሕይወት እንዲኖሩ ያደርጋል።


ድኾችን ከትቢያ ችግረኞችንም ከዐመድ ቊልል ያነሣቸዋል።


የማይለወጥ እውነተኛ የተስፋ ቃል ስሰጥ በራሴ ምዬ ነው። ስለዚህ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ አንደበትም ሁሉ በእኔ ስም ይምላል።


ሕዝቦች በብርሃንዋ ይመላለሳሉ፤ የምድር ነገሥታትም ክብራቸውን ወደ እርስዋ ያመጣሉ፤


በወልድ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቊጣ በእርሱ ላይ ይኖርበታል እንጂ ሕይወትን አያገኝም።


“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በእኔ በምረዳችሁ ላይ ስለ ተነሣችሁ አጠፋችኋለሁ፤


ልጆች የእናታቸውን ጡት እንደሚጠቡ የአንቺም ልጆች የሕዝቦችንና የነገሥታትን ሀብት በመውሰድ ይጠቀሙበታል፤ አንቺም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ ኀያሉ የያዕቆብ አምላክ መሆኔን ታውቂአለሽ።


ካለችበት ከጥልቁ ጒድጓድ ትናገራለች፤ ከታች ከትቢያ ውስጥ ንግግርዋ ይመጣል፤ ድምፅዋም እንደ ምትሐት ከምድረ በዳ ይወጣል፤ ከአዋራ ውስጥም ዝቅ ያለ ድምፅዋ ይሰማል።


ስለዚህ ጌታ የሠራዊት አምላክ በግዙፉ ሠራዊቱ ላይ የሚያመነምን በሽታ ይልክበታል፤ በሰውነቱም ውስጥ እንደ እሳት የሚያቃጥል ትኲሳት ይልክበታል።


የእግዚአብሔር ቊጣ በእነርሱ ላይ ተነሣ፤ የእስራኤልን ኀያላን ሰዎች ገደለ፤ ምርጥ ወጣቶችንም በአጭሩ ቀጨ።


አእምሮአቸው ክፉ ሐሳብን እያፈለቀ ከዐይነ ስባቸው የሚወጡት ዐይኖቻቸው አፍጥጠው ይመለከታሉ።


የዳኑት የኢየሩሳሌም ሰዎች በጽዮን ተራራ ላይ ሆነው ኤዶምን ይገዛሉ፤ መንግሥቱም የእግዚአብሔር ይሆናል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios