መዝሙር 23:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጣም ጨለማ በሆነ ሸለቆ በኩል ባልሄድም እንኳ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንክ፥ ምንም ክፉ ነገር አልፈራም። ያንተ በትርና ምርኲዝ ያጽናኑኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳ፣ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንህ፣ ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ፣ እነርሱ ያጽናኑኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፥ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልቡ ንጹሕ የሆነ፥ እጆቹም የነጹ፥ በነፍሱ ላይ ከንቱን ያልወሰደ፥ ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ። |
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።
እኔ እነርሱን ከምድረ ግብጽ አወጣኋቸው፤ በምድረ በዳ መራኋቸው፤ ጐድጓዳማ በሆነ መንገድ ድርቅና ጨለማ በበዛበት በረሓ፥ ማንም በማይኖርበትና በማይመላለስበት ምድር አሳለፍኳቸው፤ እነርሱ ግን ‘ይህን ሁሉ ያደረገልን አምላክ ወዴት ነው?’ ብለው እንኳ አልጠየቁም።
እግዚአብሔር ሆይ! የአንተ መንጋ የሆነውን ሕዝብህን በሥልጣንህ ጠብቅ፤ እነርሱም በለመለመ አትክልት ቦታ መካከል በጫካ ውስጥ ብቻቸውን የሚኖሩ ናቸው፤ እንደ ቀድሞው ዘመን በባሳንና በገለዓድ እንዲመገቡ አድርጋቸው።
ቀጥሎም “ተወዳጅ” የተባለውን በትሬን አንሥቼ ሰበርኩት፤ ይህን ማድረጌም ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ቃል ኪዳን መቋረጡን ለማመልከት ነው።
ከዚህ በኋላ “አንድነት” የተባለውን ሁለተኛውን በትር ሰበርኩት፤ ይህንንም ማድረጌ በይሁዳና በእስራኤል መካከል የነበረው ወንድማማችነት መጥፋቱን ለማመልከት ነበር።
በእነዚያ ቀኖች ዐሥር የሌላ አገር ሰዎች ወደ አንድ አይሁዳዊ ቀርበው የልብሱን ዘርፍ በመያዝ ‘እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለ ሰማን ከእናንተ ጋር እንሂድ’ ይሉታል።”
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙም ‘ዐማኑኤል’ ተብሎ ይጠራል።” ዐማኑኤል ማለትም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው።