Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 23:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ልቡ ንጹሕ የሆነ፥ እጆ​ቹም የነጹ፥ በነ​ፍሱ ላይ ከን​ቱን ያል​ወ​ሰደ፥ ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውም በሽ​ን​ገላ ያል​ማለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳ፣ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንህ፣ ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ፣ እነርሱ ያጽናኑኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፥ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በጣም ጨለማ በሆነ ሸለቆ በኩል ባልሄድም እንኳ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንክ፥ ምንም ክፉ ነገር አልፈራም። ያንተ በትርና ምርኲዝ ያጽናኑኛል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 23:4
26 Referencias Cruzadas  

እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና አት​ደ​ን​ግጥ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለሁ፤ እረ​ዳ​ህ​ማ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቄም ቀኝ ደግፌ እይ​ዝ​ሃ​ለሁ።


ትእ​ዛ​ዝ​ህን ሁሉ ስመ​ለ​ከት በዚ​ያን ጊዜ አላ​ፍ​ርም።


ከመ​ን​ፈ​ስህ ወዴት እሄ​ዳ​ለሁ? ከፊ​ት​ህስ ወዴት እሸ​ሻ​ለሁ?


ከሚ​ከ​ብ​ቡ​ኝና በእኔ ላይ ከሚ​ነሡ ከአ​እ​ላፍ አሕ​ዛብ አል​ፈ​ራም።


በጨ​ለ​ማና በሞት ጥላ ለነ​በ​ሩት ብር​ሃ​ኑን ያሳ​ያ​ቸው ዘንድ፥ እግ​ሮ​ቻ​ች​ን​ንም ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ወጣ።”


በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።


ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመንፈስህ ጋር ይሁን። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።


እነ​ር​ሱም፥ “ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን፥ በም​ድረ በዳና በባ​ድማ፥ ዕን​ጨ​ትና ውኃ፥ የእ​ን​ጨት ፍሬም በሌ​ለ​በት ምድር፥ ሰው በማ​ያ​ል​ፍ​በ​ትና የሰው ልጅም በማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​በት ምድር የመ​ራን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዴት አለ? አላ​ሉም።


ገን​ዘ​ቡን በአ​ራጣ የማ​ያ​በ​ድር፥ በን​ጹሑ ላይ መማ​ለ​ጃን የማ​ይ​ቀ​በል። እን​ዲህ የሚ​ያ​ደ​ርግ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ታ​ወ​ክም።


ጨለ​ማና የሞት ጥላ ያግ​ኙ​አት፤ ጭጋ​ግም ይም​ጣ​ባት፤


እኔም ከሕዝቦች ሁሉ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አፈርስ ዘንድ ውበት የተባለችውን በትሬን ወስጄ ቈረጥሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ታላቅ ናት፥ በፈ​ቃ​ዱም ሁሉ የተ​ፈ​ለ​ገች ናት።


የጥ​ዋት ብር​ሃን ለእ​ነ​ርሱ ሁሉ እንደ ሞት ጥላ ነው፤ የሚ​ሆ​ነ​ውን ድን​ጋጤ ያው​ቃ​ሉና። ሞት​ንም ይጠ​ራ​ጠ​ራ​ሉና።


የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ።


በይሁዳና በእስራኤል መካከል ያለውንም ወንድማማችነት እሰብር ዘንድ ማሰሪያ የተባለቸውን ሁለተኛይቱን በትሬን ቈረጥሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios