መዝሙር 149:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ሕዝቦች በድል አድራጊነታቸው ደስ ይበላቸው፤ ሌሊቱን በሙሉ በደስታ ይዘምሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅዱሳን በዚህ ክብር ይጓደዱ፤ በመኝታቸውም ላይ እልል እያሉ ይዘምሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅዱሳን በክብር ይመካሉ፥ በምንጣፋቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቃን በክብሩ ይመካሉ፤ በመኝታቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ። |
ይህም የሆነው ዘለዓለማዊው መጥቶ ለልዑል እግዚአብሔር ቅዱሳን ፍትሕ እስከ ሰጠበት ጊዜ ድረስ ነው፤ ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወርሱበት ጊዜ ደረሰ።
ወደዚህ አሁን በእምነት ጸንተን ወደምንገኝበት ጸጋ የገባነው በእርሱ ስለ ሆነ በተስፋ የእግዚአብሔር ክብር ተካፋዮች በመሆናችን እንመካለን።
ኢየሱስ ክርስቶስን ያላያችሁት እንኳ ብትሆኑ ትወዱታላችሁ፤ አሁን እንኳ የማታዩት ብትሆኑ ታምኑበታላችሁ፤ በቃላት ሊገለጥ በማይቻልና በከበረ ደስታ ደስ ይላችኋል።