ደክሞት ተስፋ በመቊረጥ ላይ ሳለ ድንገተኛ አደጋ እጥልበታለሁ፤ በዚያን ጊዜ እርሱ ድንጋጤ ላይ ይወድቃል፤ ተከታዮቹም ጥለውት ይሸሻሉ ንጉሡንም ለብቻው አግኝቼ እገድለዋለሁ፤
መዝሙር 124:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አምልጠናል፤ ወጥመዱ ተሰበረ፤ እኛም ነጻ ወጣን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፍሳችን እንደ ወፍ፣ ከዐዳኝ ወጥመድ አመለጠች፤ ወጥመዱ ተሰበረ፤ እኛም አመለጥን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች፥ ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን። |
ደክሞት ተስፋ በመቊረጥ ላይ ሳለ ድንገተኛ አደጋ እጥልበታለሁ፤ በዚያን ጊዜ እርሱ ድንጋጤ ላይ ይወድቃል፤ ተከታዮቹም ጥለውት ይሸሻሉ ንጉሡንም ለብቻው አግኝቼ እገድለዋለሁ፤
“በሕዝቤ መካከል የሚኖሩ ክፉ ሰዎች አሉ፤ እነርሱም ወፎችን በወጥመድ እንደሚይዝ ሰው ናቸው፤ ስለዚህ ሰዎችን ለማጥመድ መረባቸውን ዘርግተው ያደባሉ።
ስለዚህም ሳኦል ዳዊትን የማሳደድ ተግባሩን አቁሞ ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ሄደ፤ ያም ቦታ “የማምለጥ አለት” ተብሎ የተጠራበት ምክንያት ይኸው ነው።
ማንም ሰው በአንተ ላይ አደጋ ጥሎ ሊገድልህ ቢፈልግ አንድ ሰው ውድ የሆነ ሀብቱን እንደሚጠብቅ አምላክህ እግዚአብሔር አንተን በሰላም ይጠብቅሃል፤ ስለ ጠላቶችህም የሆነ እንደ ሆነ አንድ ሰው ድንጋዩን ከወንጭፍ እንደሚያስፈነጥር እግዚአብሔር ራሱ አሽቀንጥሮ ይጥላቸዋል።