ስለዚህ ያዕቆብ ለቤተሰቡና አብረውት ለነበሩት ሰዎች ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ንጹሕ ልብስም ልበሱ፤
መዝሙር 116:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጩኸቴንና ልመናዬን ስለ ሰማ እግዚአብሔርን እወደዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልመናዬን ድምፅ ሰምቷልና፣ እግዚአብሔርን ወደድሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሃሌ ሉያ! ጌታ የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድሁት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብ ሁላችሁ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት፥ ወገኖችም ሁሉ ያመስግኑት፤ |
ስለዚህ ያዕቆብ ለቤተሰቡና አብረውት ለነበሩት ሰዎች ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ንጹሕ ልብስም ልበሱ፤
“በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም እጠብቀዋለሁ።
እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ ስለ ረዳቸው ከነዓናውያንን ድል ነሥተው ያዙ፤ ስለዚህ እስራኤላውያን እነርሱንና ከተሞቻቸውን ፈጽመው ደመሰሱ፤ ፈጽሞ የተደመሰሱ መሆናቸውንም ለማመልከት ያን ስፍራ “ሖርማ” ብለው ሰየሙት።
ስለዚህ ሰው በፍጹም ልቡ፥ [በፍጹም ነፍሱ፥] በፍጹም ሐሳቡ፥ በፍጹም ኀይሉ እግዚአብሔርን መውደድ ይገባዋል፤ እንዲሁም ጐረቤትን እንደ ራሱ አድርጎ መውደድ ይገባዋል፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌላም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ከማቅረብ ይልቅ እነዚህን ሁለቱን ትእዛዞች መጠበቅ ይበልጣል።”
ሦስተኛ ጊዜም “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ትወደኛለህን?” አለው። ሦስተኛ ጊዜ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና “ጌታ ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፥ እኔ እንደምወድህም ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “በጎቼን አሰማራ፤
ሐናም ዔሊን እንዲህ አለችው፤ “ጌታዬ ሆይ፥ ዕድሜህን ያርዝመውና አንድ ጊዜ እዚህ በፊትህ ቆሜ ወደ እግዚአብሔር ስጸልይ ያየኸኝ ሴት እኔ ነኝ፤