ሁሉም በተሰበሰቡ ጊዜ ዳዊት ተነሥቶ፥ እንዲህ አለ፦ “ወገኖቼ ሆይ፥ አድምጡኝ፤ ለአምላካችን የእግር ማሳረፊያ ይሆን ዘንድ የተቀደሰው ታቦት የሚያርፍበት ቤት ለመሥራት ፈልጌ ነበር፤ ለቤተ መቅደሱም ሕንጻ ማሠሪያ የሚሆነውን ዕቃ ሁሉ አዘጋጅቼአለሁ፤
መዝሙር 110:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለጌታዬ (ለመሲሑ) “ጠላቶችህን በእግርህ ማረፊያ ሥር እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ጌታዬን፣ “ጠላቶችህን ለእግርህ መረገጫ፣ እስከማደርግልህ ድረስ፣ በቀኜ ተቀመጥ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊት መዝሙር። ጌታ ጌታዬን፦ “ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ በቅኖች ሸንጎ በጉባኤም በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ። |
ሁሉም በተሰበሰቡ ጊዜ ዳዊት ተነሥቶ፥ እንዲህ አለ፦ “ወገኖቼ ሆይ፥ አድምጡኝ፤ ለአምላካችን የእግር ማሳረፊያ ይሆን ዘንድ የተቀደሰው ታቦት የሚያርፍበት ቤት ለመሥራት ፈልጌ ነበር፤ ለቤተ መቅደሱም ሕንጻ ማሠሪያ የሚሆነውን ዕቃ ሁሉ አዘጋጅቼአለሁ፤
የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚመራ እርሱ ነው፤ የንጉሥነትን ክብር በመቀዳጀት በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይገዛል፤ አንድ ካህን በዙፋኑ አጠገብ ይቆማል፤ ሁለቱም አብረው በስምምነትና በሰላም ይሠራሉ።’
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “አንተ እንዳልከው ነው፤ ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኀያሉ እግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ታዩታላችሁ፤ እንዲሁም በሰማይ ደመና ሆኖ ሲመጣ ታዩታላችሁ እላችኋለሁ።”
እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም ትክክል ነው። በኀያል ቃሉ ዓለምን ሁሉ ደግፎ ይዞአል፤ ሰዎችንም ከኃጢአት ካነጻ በኋላ በሰማይ በኀያሉ እግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦአል።
የምንሮጠውም የእምነታችን መሥራችና ፈጻሚ የሆነውን ኢየሱስን በመመልከት ነው፤ እርሱ በፊቱ በተደቀነው ደስታ ምክንያት በመስቀል ላይ የመሞትን ውርደት ከምንም ሳይቈጥር የመስቀልን መከራና ሞት ታገሠ፤ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝም ተቀመጠ።
እንግዲህ ከምንነጋገርባቸው ነገሮች ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማይ በልዑል እግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ የካህናት አለቃ አለን፤