ምሳሌ 29:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰው የገዛ ኃጢአቱ ወጥመድ ሆኖ ይይዘዋል፥ ደግ ሰው ግን እየዘመረ ሐሤትን ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሰው በራሱ ኀጢአት ይጠመዳል፤ ጻድቅ ግን ይዘምራል፤ ደስም ይለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ ሰው በጥፋቱ ይጠመዳል፥ ጻድቅ ግን ደስ ይለዋል፥ እልልም ይላል። |
ከዚህ በኋላ ሙሴና የእስራኤል ሕዝብ ከዚህ የሚከተለውን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፦ “ፈረሱንና ፈረሰኛውን ወደ ባሕር በመጣል፥ ክብር የተሞላው ድል ስለ ተጐናጸፈ፥ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።
ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ሰው ይህ መጥፎ ዕድል መቼ እንደሚገጥመው አያውቅም፤ ወፍ በራ በወጥመድ ውስጥ እንደምትገባ፥ ዓሣም በመጥፎ አጋጣሚ በመረብ እንደሚያዝ እንዲሁም የሰው ልጅ ሁሉ ሳያስበው ድንገት በሚደርስበት በክፉ አጋጣሚ ይጠመዳል።
ኢየሱስ ክርስቶስን ያላያችሁት እንኳ ብትሆኑ ትወዱታላችሁ፤ አሁን እንኳ የማታዩት ብትሆኑ ታምኑበታላችሁ፤ በቃላት ሊገለጥ በማይቻልና በከበረ ደስታ ደስ ይላችኋል።