Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 29:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ደግ ሰው ስለ ድኾች መብት ይቈረቈራል፤ ክፉ ሰው ግን ለእንደዚህ ዐይነቱ ነገር ግድ አይኖረውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ጻድቅ ስለ ድኾች ፍትሕ ያውቃል፤ ክፉ ግን ደንታ የለውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጻድቅ የድሆችን መብት ይመለከታል፥ ክፉ ሰው ግን ይህንን አያስተውልም።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 29:7
16 Referencias Cruzadas  

ለድኾች አባት፥ ለማላውቃቸውም ሰዎች ጠበቃ ነበርኩ።


“ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቼ አቤቱታ አቅርበውልኝ አቤቱታቸውን ሳልቀበል ቀርቼ እንደ ሆነ፥


በፍርድ ሸንጎ ተሰሚነት ያለኝ መሆኔን በማወቄ በሙት ልጅ ላይ እጄን አንሥቼ አላውቅም።


ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ፤ መከራዬን አይተህ ጭንቀቴን ታውቃለህ፤


ድኾችን የሚረዱ የተባረኩ ናቸው፤ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ እግዚአብሔር ይረዳቸዋል።


ወደ እርሱ የሚጮኹትን ድኾች፥ ችግረኞችንና የተጨቈኑትን ሰዎች ነጻ ያወጣል።


የድኾችን ጩኸት ለመስማት ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው እርሱም ተቸግሮ በሚጮኽበት ጊዜ የሚረዳው አያገኝም።


እነርሱ እንደ ቅልብ ሰንጋ ወፍረዋል፤ ክፉ ሥራቸውም ገደብ የለሽ ሆኖአል፤ እናትና አባት የሌላቸውን ልጆች መብት አያስከብሩም፤ ለችግረኞችም ትክክለኛ ፍርድ አይፈርዱም።


በውስጥሽም አባትና እናት ይናቃሉ፤ የውጪ አገር ሰዎች ይታለላሉ፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶችና አባትና እናት የሌላቸው ልጆች ይበደላሉ።


ወንድሞች ሆይ! ሰው ተሳስቶ አንዳች ጥፋት አድርጎ ቢገኝ መንፈሳውያን የሆናችሁት እናንተ እንዲህ ዐይነቱን ሰው በገርነት አቅኑት፤ ነገር ግን አንተም በዚህ ዐይነት ፈተና እንዳትወድቅ ተጠንቀቅ።


የናባልን ጉዳይ ከቁም ነገር አታግባው! እርሱ ልክ እንድ አስሙ አጠራር ሞኝ ነው! ጌታዬ፥ የአንተ አገልጋዮች በመጡ ጊዜ እኔ በዚያ አልነበርኩም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos