ምሳሌ 15:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተግሣጽን የሚጠላ ራሱን ይጐዳል። ተግሣጽን የሚቀበል ግን ጥበብን ይጨምራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተግሣጽን የሚንቅ ራሱን ይንቃል፤ ዕርምትን የሚቀበል ግን ማስተዋልን ያገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተግሣጽን ቸል የሚል የራሱን ነፍስ ይንቃል፥ ዘለፋን የሚሰማ ግን አእምሮ ያገኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተግሣጽ የሚከላከል ራሱን ይጠላል። ተግሣጽን የሚወድድ ግን ራሱን ይወድዳል። |
ለሚመለከታቸው ሰው ፊታቸው ይመሰክርባቸዋል፤ እንደ ሰዶም ሰዎች ሳይደብቁ ኃጢአታቸውን በግልጽ ይናገራሉ፤ በራሳቸው ላይ ጥፋትን ስላመጡ ወዮላቸው።
እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።
በሚያስፈርዱበትም ጊዜ እንዲህ ይበሉ፥ ‘እነሆ፥ ይህ ልጃችን እልኸኛና ዐመፀኛ ነው፤ ለእኛ መታዘዝን እምቢ ብሎአል፤ ሰካራምና ገንዘብ አባካኝ ሆኖብናል፤’
ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት ተጠንቀቁ፤ እንዲሁም ምንም መራራ ፍሬ የሚያፈራ ሥር በመካከላችሁ እንዳይበቅልና እንዳያስቸግራችሁ ብዙዎችንም እንዳያረክስ ተጠንቀቁ።