Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 17:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሞኝ የተፈጥሮ ማስተዋል ስለሌለው ገንዘቡን ጥበብን ለማግኘት ቢያውል ምንም አይጠቅመውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ጥበብን ለማግኘት ፍላጎት ስለሌለው፣ ሞኝ እጅ የገባ ገንዘብ ጥቅሙ ምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በሰነፍ እጅ የጥበብ መግዣ ገንዘብ መኖሩ ስለ ምንድነው? ጥበብን ይገዛ ዘንድ አእምሮ የለውምና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ለአላዋቂ ሰው ገንዘብ ለምንድን ነው? አላዋቂ ሰው ጥበብን ገንዘብ ማድረግ አይችልምና፥ ቤቱን የሚያስረዝም ሰው ለራሱ ጥፋትን ይሻል፤ ለመማርም የሚጨንቀው ወደ ክፉ ይወድቃል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 17:16
16 Referencias Cruzadas  

እውነትን፥ ጥበብን፥ ተግሣጽን፥ ማስተዋልን ገንዘብ አድርጋቸው እንጂ አትተዋቸው።


የጥበበኛ ሰው ልብ ዕውቀትን ገንዘብ ያደርጋል፤ የአስተዋዮችም ጆሮ ጥበብን ይፈልጋል።


ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ እንደ መሆናችን የተቀበላችሁትን ጸጋ በከንቱ አታስቀሩት ብለን እንለምናችኋለን።


ሁልጊዜ በዚህ ዐይነት ቢያስቡማ እንዴት መልካም ነበር! ሁልጊዜ ቢያከብሩኝና ትእዛዞቼንም ሁሉ ቢፈጽሙ ሁሉ ነገር ለእነርሱና ለዘሮቻቸው ለዘለዓለም በመልካም ሁኔታ በተከናወነላቸው ነበር።


ጳውሎስና በርናባስ ግን እንዲህ ሲሉ በድፍረት ተናገሩ፤ “የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ ለእናንተ እንዲነገር አስፈላጊ ነው፤ እናንተ አንቀበልም ካላችሁና የዘለዓለም ሕይወት እንደማይገባችሁ በራሳችሁ ከፈረዳችሁ ግን እነሆ፥ እኛ ዞር ብለን ወደ አሕዛብ እንሄዳለን።


ክፉ ነገር የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላል፤ ክፉ ሥራውም እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የዝሙት ሥራ፥ የቈየና አዲስ የወይን ጠጅን መከተል የሕዝቤን አእምሮ አጥፍቶአል።


ፌዘኛ ሰው ጥበብን ይፈልጋል፤ አያገኛትም። አስተዋዮች ግን ዕውቀትን በቀላሉ ይገበያሉ።


ማስተዋል የጐደለው ሰው ጥበብን መገንዘብ አይችልም፤ ሰዎች ቁም ነገር ባለው ጉዳይ ላይ ሲወያዩ እርሱ የሚያቀርበው አስተያየት የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios