Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 13:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ትምህርት የማይወድ ሰው፥ ድኽነትና ውርደት ይገጥመዋል፤ ተግሣጽን የሚቀበል ግን ይከበራል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ተግሣጽን የሚንቅ ወደ ድኽነትና ኀፍረት ይሄዳል፤ ዕርምትን የሚቀበል ሁሉ ግን ይከበራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ድህነትና ነውር ተግሣጽን ቸል ለሚሉ ነው፥ ዘለፋን የሚሰማ ግን ይከብራል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ትምህርት ድህነትንና ጕስቍልናን ያስወግዳል፤ ተግሣጽን የሚጠብቅ ግን ይከብራል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 13:18
15 Referencias Cruzadas  

ሞኝ የአባቱን ምክር ይንቃል፤ ተግሣጽን የሚቀበል ግን አስተዋይ ነው።


ዕውቀትን የሚወድ ሰው ከስሕተት መታረምን ይወዳል፤ ተግሣጽን የሚጠላ ግን ጅል ሰው ነው።


ለማዳመጥ ፈቃደኛ ለሆነ ሰው ብልኅ ሰው የሚሰጠው ተግሣጽ ከወርቅ ጉትቻ ወይም ከጥሩ ወርቅ ከተሠራ ጌጥ ይበልጥ የተወደደ ይሆንለታል።


መልካም ምክርን የሚንቅ ችግር ይደርስበታል፤ ትእዛዝን የሚያከብር ግን ዋጋ ያገኝበታል።


ብዙ ሰዎች የለጋሥ ሰውን ወዳጅነት ይፈልጋሉ፤ ስጦታን ለሚሰጥ ሰው ሁሉም ወዳጁ ነው።


ጠቢብን አስተምረው፥ በይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ ደግን ሰው አስተምረው፤ ዕውቀትን ይጨምራል።


ያንን የሚናገረውን አንቀበልም እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ እግዚአብሔር በሰው አማካይነት ከምድር ሲናገራቸው አንሰማም ያሉት ካላመለጡ፥ ታዲያ እኛ ከሰማይ የሚናገረንን ባንቀበል እንዴት እናመልጣለን!


ደግ ሰው በቅንነት መንፈስ ሊቀጣኝና ሊገሥጸኝ ይችላል፤ ከክፉ ሰዎች ግን ክብርን እንኳ አልቀበልም፤ ዘወትርም ክፉ ሥራቸውን በመቃወም እጸልያለሁ።


የተመኙትን ነገር ማግኘት እጅግ ደስ ያሰኛል፤ ማስተዋል የጐደላቸው ሰዎች ግን ከክፉ ነገር መራቅ አይፈልጉም።


እውነተኞች ሊበሉ የሚፈልጉትን ያኽል ያገኛሉ። ኃጢአተኞች ግን ዘወትር ይራባሉ።


የሞኞችን ዘፈን ከመስማት የጥበበኞችን ተግሣጽ መስማት ይሻላል።


እኛና የቀድሞ አባቶቻችን በመደጋገም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔር አምላካችንን አሳዝነናል፤ ትእዛዞቹንም አልፈጸምንም፤ ስለዚህ በዕፍረት ልንወድቅና ውርደትም እንደ ልብስ ሊሸፍነን ይገባል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios