Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 15:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ሕይወት የሚሰጥ ምክር የሚቀበል የጠቢባን ጓደኛ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ሕይወት ሰጪ የሆነውን ተግሣጽ የሚሰማ፣ በጠቢባን መካከል ይኖራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 የሕይወትን ተግሣጽ የሚሰማ ጆሮ በጠቢባን መካከል ይኖራል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 የብልህን ተግሣጽ የሚሰማ ሰው ከጠቢባን ጋራ አንድ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 15:31
14 Referencias Cruzadas  

ሞኝ የአባቱን ምክር ይንቃል፤ ተግሣጽን የሚቀበል ግን አስተዋይ ነው።


ለማዳመጥ ፈቃደኛ ለሆነ ሰው ብልኅ ሰው የሚሰጠው ተግሣጽ ከወርቅ ጉትቻ ወይም ከጥሩ ወርቅ ከተሠራ ጌጥ ይበልጥ የተወደደ ይሆንለታል።


ምክርን ብትሰማና ለመማርም ፈቃደኛ ብትሆን የኋላ ኋላ ጥበብ መገብየትህ አይቀርም።


ከጥበበኞች የሚወዳጅ ጥበበኛ ይሆናል። ማስተዋል ከጐደላቸው ሰዎች ጋር ጓደኛ የሚሆን ግን ይጐዳል።


ተግሣጼን ብትቀበሉ ሐሳቤን በገለጥሁላችሁ ነበር፤ ቃሌንም እንድታውቁ ባደረግሁ ነበር።


እነርሱ የወጡት ከእኛ መካከል ነው። ይሁን እንጂ ዱሮውንም ከእኛ ወገን አልነበሩም። ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋርም ጸንተው በኖሩ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ከእኛ ወገን አለመሆናቸው እንዲታወቅ ከእኛ መካከል ተለይተው ወጥተዋል።


“ጆሮአችሁን አዘንብላችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ቃሌን አድምጡ፤ ዳዊትን እንደ ወደድኩት እናንተን በታማኝነት ለመውደድ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ።


በፈገግታ የተሞላ ፊት ልብን ያስደስታል፤ የምሥራች ቃልም አጥንትን ያለመልማል።


ተግሣጽን የሚጠላ ራሱን ይጐዳል። ተግሣጽን የሚቀበል ግን ጥበብን ይጨምራል።


የጥበበኛ ሰው ልብ ዕውቀትን ገንዘብ ያደርጋል፤ የአስተዋዮችም ጆሮ ጥበብን ይፈልጋል።


የሞኞችን ዘፈን ከመስማት የጥበበኞችን ተግሣጽ መስማት ይሻላል።


ትምህርት የማይወድ ሰው፥ ድኽነትና ውርደት ይገጥመዋል፤ ተግሣጽን የሚቀበል ግን ይከበራል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios