ምሳሌ 13:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ መልእክተኛ ችግርን ያመጣል፤ ታማኝ መልእክተኛ ግን ሰላምን ያስገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ መልእክተኛ መከራ ውስጥ ይገባል፤ ታማኝ መልእክተኛ ግን ፈውስን ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጥፎ መልእክተኛ በክፉ ላይ ይወድቃል፥ የታመነ መልእክተኛ ግን ፈውስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰነፍ መልእክተኛ በክፉ ላይ ይወድቃል፤ ብልህ መልእክተኛ ግን ራሱን ያድናል። |
ሕልም ያለመ ነቢይ ቢኖር ሕልሙን ብቻ ይናገር፤ ቃሌን የሰማ ነቢይ ግን ያንኑ ቃል በታማኝነት ይናገር፤ ገለባ ከስንዴ ጋር ምን ግንኙነት አለው?
እኔ አንድን በደለኛ በኃጢአቱ ምክንያት በእርግጥ ትሞታለህ ብለው አንተ ግን ያን ሰው ከኃጢአቱ ተመልሶ ይድን ዘንድ ባታስጠነቅቀው እርሱ በኃጢአቱ ይሞታል፤ ስለ እርሱ ሞት ግን አንተን ተጠያቂ አደርግሃለሁ።
እኛ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ንግድ ዕቃ እንደሚቸረችሩት እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላኩ ቅን መልእክተኞች በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት እንናገራለን።
እግዚአብሔር ሰዎችን በእኛ አማካይነት ስለሚጠራ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ ስለዚህ “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ!” ብለን በክርስቶስ ስም እንለምናችኋለን።