ፊልጵስዩስ 3:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ እግዚአብሔርን በመንፈስ የምናመልክና በውጭ በሚታየው ሥርዓት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ የምንመካ ስለ ሆንን በእውነት ተገርዘናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ በእውነት የተገረዝን በእግዚአብሔር መንፈስ የምናመልክ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ የምንመካ፣ በሥጋም የማንታመን ነንና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን በእውነትም ከተገረዙት ወገን የሆንን ነንና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግዙራንስ እግዚአብሔርን በመንፈስ የምናገለግለውና የምናመልከው እኛ ነን፤ እኛም በኢየሱስ ክርስቶስ እንመካለን እንጂ በሥጋችን የምንመካ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን እኛ የተገረዝን ነንና። |
እናንተ የይሁዳ ሕዝብና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሆይ! የልባችሁን ክፋት ገርዛችሁ አእምሮአችሁን በማንጻት ሁለንተናችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ይህን ባታደርጉ ግን በክፉ ሥራችሁ ምክንያት ቊጣዬ እንደ እሳት ይነዳል፤ ቊጣዬም ከነደደ ማንም ሊያጠፋው አይችልም።”
የግብጽ፥ የይሁዳ፥ የኤዶም፥ የአሞን፥ የሞአብና በበረሓ ጠረፍ የሚኖሩ የግንባራቸውን ግራና ቀኝ ጠጒር የተላጩ ሕዝቦች እንዲሁም የእስራኤል ሕዝብ ከልባቸው ያልተገረዙ ስለ ሆኑ ሁሉንም በአንድ ዐይነት እቀጣለሁ።”
እነሆ፥ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ዳር እስከ ዳር ለእኔ ክብር ይሰጣሉ፤ በየትኛውም ስፍራ ለእኔ ዕጣን እያጠኑ ንጹሕ መሥዋዕት ያቀርቡልኛል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያከብሩኛል።
አሁን ግን አስሮን ከነበረው ሕግ በሞት የመለየት ያኽል ስለ ተለየን ከሕግ እስራት ነጻ ወጥተናል፤ ስለዚህ ከእንግዲህ የምናገለግለው በአዲሱ መንፈሳዊ መመሪያ እንጂ አስቀድሞ በተጻፈው በአሮጌው የሕግ መመሪያ አይደለም።
ስለዚህ “አባ! አባታችን ሆይ!” ብላችሁ የምትጠሩበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ በፍርሃት ለመኖር እንደገና የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁም።
ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ማንኛውም ፍጥረት ቢሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካገኘነው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን የሚችል ምንም ነገር እንደሌለ እርግጠኛ ነኝ።
አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተና ለልጆችህ ታዛዥ ልብ ይሰጣል፤ ስለዚህም እርሱን በፍጹም ልብህ ትወደዋለህ፤ በዚያችም ምድር በሕይወት ትኖራለህ።
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋዮች ከሆኑት ከጳውሎስና ከጢሞቴዎስ፥ በፊልጵስዩስ ከተማ ለሚኖሩ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን ለሆኑ ሁሉ፥ እንዲሁም ለኤጲስ ቆጶሳትና ዲያቆናት፦
ይህን ሁሉ ገና አላገኘሁም፤ ወይም በዚህ ሁሉ ፍጹም ሆኜአለሁ ለማለት አልችልም፤ ይሁን እንጂ ኢየሱስ ክርስቶስ እኔን የእርሱ አድርጎ ያዘጋጀልኝን ሽልማት ለማግኘት ወደፊት በመሮጥ እተጋለሁ።
ሽልማቴንም ለማግኘት በፊቴ ወዳለው ግብ እሮጣለሁ፤ ይህም ሽልማት እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ወደ ላይ ጠርቶ የሚሰጠኝ ሕይወት ነው።
በእርሱም በማመናችሁ ተገርዛችኋል፤ ይህም መገረዛችሁ ኃጢአተኛውን የሥጋ ባሕርይ ለማስወገድ በክርስቶስ የተደረገ ነው እንጂ በሰው እጅ የተደረገ አይደለም።