La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 14:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሕዝቡም ሌሊቱን ሁሉ በመጨነቅ ሲጮኹ አደሩ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያች ሌሊት ማኅበረ ሰቡ ሁሉ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸና አለቀሰ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ማኅበሩም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ጮኹ፤ በዚያም ሌሊት ሕዝቡ አለቀሰ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን አን​ስ​ተው ጮኹ፤ ሕዝ​ቡም ሌሊ​ቱን ሁሉ አለ​ቀሱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ማኅበሩም ሁሉ ድምፃቸውን አንሥተው ጮኹ፤ ሕዝቡም በዚያ ሌሊት አለቀሱ።

Ver Capítulo



ዘኍል 14:1
13 Referencias Cruzadas  

በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው አጒረመረሙ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል አንሰማም አሉ።


ይህም ሁሉ ሆኖ ሕዝቡ ኃጢአት ከመሥራት ገና አልተገታም፤ ብዙ ተአምራት ቢያሳያቸውም በእርሱ አላመኑም።


የግብጽ ንጉሥ ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ቅርብ በሆነው በፍልስጥኤም የባሕር ጠረፍ በኩል ባለው መንገድ አልመራቸውም፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ሕዝቡ ከፊት ለፊታቸው ጦርነት እንደሚጠብቃቸው በሚያዩበት ጊዜ ሐሳባቸውን ለውጠው ወደ ግብጽ እንዳይመለሱ ነው።


ሰዎቹም ይህን የሚያሳዝን ቃል በሰሙ ጊዜ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ምንም ዐይነት ጌጣጌጥ ማድረግ አልፈለጉም።


ከአሴር ነገድ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፥


በዚያም ከኔፊሊም ወገን የሆኑትን የዐናቅን ዘሮች አይተናል፤ እኛ በእነርሱ ፊት ልክ እንደ ፌንጣ ያኽል ሆነን ነበር የታየነው፤ እነርሱም እንደዚያው አድርገው ሳይመለከቱን አይቀሩም” አሉ።


በሙሴና በአሮንም ላይ እንዲህ እያሉ አጒረመረሙ፥ “በግብጽ ሳለን ወይም በዚህ ምድረ በዳ ሞተን በቀረን መልካም በሆነ ነበር!


“ነገር ግን እናንተ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ በማመፅ ወደዚያች ምድር መግባትን አልወደዳችሁም።


ስለዚህም ይረዳችሁ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በመጮኽ አለቀሳችሁ፤ ነገር ግን ጩኸታችሁን ሊያዳምጥና ሊረዳችሁ አልወደደም።


እግዚአብሔር፥ ‘ሂዱ፤ የሰጠኋችሁንም የተስፋ ምድር ውረሱ’ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁም ጊዜ በእርሱ ላይ ዐመፃችሁ እንጂ አልተማመናችሁበትም፤ ለቃሉም አልታዘዛችሁም።


ከእኔ ጋር ሄደው የነበሩ ሰዎች ግን የሕዝቡ ልብ በፍርሃት እንዲቀልጥ አደረጉ፤ እኔ ግን ለአምላኬ ለእግዚአብሔር በታማኝነት ታዛዥ ሆኛለሁ፤


ዳዊትና ተከታዮቹም ፈጽሞ እስኪደክሙ ድረስ ባለማቋረጥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ።