ከዚያ በኋላ አብርሃም ለእግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቤሜሌክንና ሚስቱን፥ ሴቶች አገልጋዮቹንም ፈውሶአቸው ልጆች እንዲወልዱ አድርጎአቸዋል፤
ዘኍል 12:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሙሴ “እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ ፈውሳት” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ሙሴ፣ “አምላክ ሆይ፤ እባክህ ፈውሳት” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም እንዲህ ብሎ ወደ ጌታ ጮኸ፦ “አቤቱ፥ እባክህ፥ ፈውሳት።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ወደ እግዚአብሔር እየጮኸ፥ “አቤቱ፥ እባክህ፥ አድናት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ወደ እግዚአብሔር እየጮኸ፦ አቤቱ፥ እባክህ፥ አድናት አለው። |
ከዚያ በኋላ አብርሃም ለእግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቤሜሌክንና ሚስቱን፥ ሴቶች አገልጋዮቹንም ፈውሶአቸው ልጆች እንዲወልዱ አድርጎአቸዋል፤
ንጉሡ ኢዮርብዓም “እባክህ እጄን ያድንልኝ ዘንድ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልኝ!” ሲል የእግዚአብሔርን ነቢይ ለመነው። የእግዚአብሔርም ነቢይ ወደ እግዚአብሔር ጸልዮለት የንጉሡ እጅ ዳነች። እንደ ቀድሞም ሆነች።
እንዲህም አላቸው፤ “በጥሞና ትእዛዞቼን ብታዳምጡና በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር በታዛዥነት ብታደርጉ፥ ኅጎቼንም ሁሉ ብትጠበቁ፥ በግብጻውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች በአንዱ እንኳ አልቀጣችሁም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
እግዚአብሔርም “እጅህን እንደገና ወደ ብብትህ አስገባ” አለው። ሙሴም እጁን ወደ ብብቱ አስገባ፤ መልሶም ባወጣው ጊዜ ተመልሶ እነሆ፥ እንደ ሌላው ሰውነቱ ጤናማ ሆነ።
በዚያን ጊዜ ጨረቃ እንደ ፀሐይ ትደምቃለች፤ የፀሐይም ብርሃን ከቀድሞ ሰባት እጅ የበለጠ ይሆናል፤ የሰባት ቀን ብርሃን ያኽልም ድምቀት ይኖረዋል፤ ይህም ሁሉ የሚሆነው እግዚአብሔር ራሱ በሕዝቡ ላይ ያመጣባቸውን ቊስል ጠግኖ በሚፈውስበት ቀን ነው።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፦ “አባት ሆይ! የሚያደርጉትን ስለማያውቁ ይቅር በላቸው!” አለ። ወታደሮቹም ዕጣ ተጣጥለው የኢየሱስን ልብስ ተከፋፈሉ።
እንዲህ ዐይነቱ በእምነት ላይ የተመሠረተ ጸሎት በሽተኛውን ያድነዋል፤ ጌታም ከበሽታው ይፈውሰዋል፤ የሠራው ኃጢአትም ቢኖር ይቅር ይባልለታል።
“ሳኦል እኔን ትቶአል፤ ትእዛዜንም ስላልጠበቀ እርሱን በማንገሤ ተጸጸትሁ፤” ሳሙኤልም በዚህ ነገር ተቈጥቶ ሌሊቱን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር በመጮኽ ማለደ፤