ይኸውም እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳትመርጥ በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤
ዘኍል 12:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ከኩሽ ነገድ የሆነች (ኢትዮጵያዊት) ሴት በማግባቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በሐሜት እንዲህ ሲሉ ነቀፉት፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ኢትዮጵያዊት ሴት አግብቶ ነበርና ባገባት ኢትዮጵያዊት ምክንያት ማርያምና አሮን ይነቅፉት ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ኢትዮጵያይቱን በእርግጥ አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ኢትዮጵያዊቱን ሴት አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያዊቱ ሴት ምክንያት ማርያምና አሮን አሙት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ። |
ይኸውም እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳትመርጥ በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤
ርብቃ ይስሐቅን “ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሒታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱን ካገባ ከመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ” አለችው።
ፈርዖን ለዮሴፍ “ጻፍናት ፐዕናሕ” የሚል መጠሪያ ስም አወጣለት፤ አስናት ተብላ የምትጠራውን የጶጢፌራን ልጅ በሚስትነት ሰጠው፤ ጶጢፌራ ኦን ተብሎ በሚጠራው ከተማ ካህን ነበር።
አንድ የምድያም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ውሃ ለመቅዳትና በገንዳ እየሞሉ የአባታቸውን በጎችና ፍየሎች ለማጠጣት ወደዚያ መጡ።
ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆቻችሁ ሚስቶች ብታደርጉ የእነዚያ ሴቶች ልጆች ጣዖት ማምለክን ስለሚከተሉ የእናንተንም ወንዶች ልጆች ጣዖት አምልኮን እንዲከተሉ ያደርጓቸዋል።
ባልዋ የሞተባትን ወይም አግብታ የተፋታችውን ወይም ክብረ ንጽሕናዋ የተደፈረውን፥ ወይም አመንዝራ የነበረችውን ሴት አያግባ፤ ድንግል የሆነችውን ብቻ ወገኑ ከሆኑ ሕዝብ መካከል መርጦ ያግባ።
ከእነዚህ ሕዝብ አንዱም ወደዚያች ምድር ለመግባት በሕይወት አይኖርም፤ በግብጽ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግኋቸውን ተአምራት ሁሉ አይተዋል፤ ነገር ግን የትዕግሥቴን ብዛት ደጋግመው በመፈታተን ለእኔ መታዘዝ እምቢ አሉ።
ዓሞራም በግብጽ የተወለደችውን የሌዊን ሴት ልጅ ዮኬቤድን አግብቶ ነበር፤ እርስዋም አሮንና ሙሴ የተባሉትን ሁለት ወንዶች ልጆችንና ማርያም የተባለችውን አንዲት ሴት ልጅ ወለደችለት።