Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 12:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሙሴ ኢትዮጵያዊት ሴት አግብቶ ነበርና ባገባት ኢትዮጵያዊት ምክንያት ማርያምና አሮን ይነቅፉት ጀመር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሙሴም ኢትዮጵያይቱን በእርግጥ አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ሙሴ ከኩሽ ነገድ የሆነች (ኢትዮጵያዊት) ሴት በማግባቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በሐሜት እንዲህ ሲሉ ነቀፉት፦

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ሙሴም ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ዊ​ቱን ሴት አግ​ብ​ቶ​አ​ልና ባገ​ባት በኢ​ት​ዮ​ጵ​ያ​ዊቱ ሴት ምክ​ን​ያት ማር​ያ​ምና አሮን አሙት።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 12:1
19 Referencias Cruzadas  

እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤


ጌታዬም እንዲህ ሲል አማለኝ፦ እኔ ካለሁበት አገር ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች ለልጄ ሚስትን አትውሰድ፤


ርብቃም ይስሐቅን አለችው፦ ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት ያዕቆብ ከዚህ አገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለምኔ ነው?


ፈርዖንም የዮሴፍን ስም ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ጠራው የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ የምትሆን አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በግብፅ ምድር ሁሉ ወጣ።


ለምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ፤ የአባታቸውንም በጎች ሊያጠጡ የውኃውንም ገንዳ ሞሉ።


ሙሴም ከዚያ ሰው ጋር ሊቀመጥ ወደደ፤ ልጁንም ሲፓራን ለሙሴ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው።


ሴት ልጆቻቸውንም ከወንድ ልጆችህ ጋር እንዳታጋባ፥ ልጆቻቸውም አምላኮቻቸውን ተከትለው ሲያመነዝሩ ከአምላኮቻቸው በኋላ ሄደው አመንዝረውም ልጆችህን እንዳያስቱ ተጠንቀቅ።


ባልዋ የሞተባትን፥ ወይም የተፋታችውን፥ ወይም ጋለሞታይቱን አያግባ፤ ነገር ግን ከሕዝቡ ድንግሊቱን ያግባ።


በግብፅ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ተአምራቴንና ክብሬን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ አሥር ጊዜ ስለ ተፈታተኑኝ፥


ከእስራኤልም ልጆች ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች ከእነርሱ ጋር ወሰዱ፤ ከጉባኤው የተመረጡ ዝናቸውም የተሰማ የማኅበሩ አለቆች ነበሩ።


የእንበረም ሚስት ስም ዮካብድ ነበረ። እርስዋ በግብፅ ከሌዊ የተወለደች የሌዊ ልጅ ነበረች፤ ለእንበረምም አሮንንና ሙሴን እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት።


ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል።


እርሱ ግን ለነገረው መልሶ፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው።


ባርያ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኋችሁን ቃል አስቡ። እኔን አሳደውኝ እንደ ሆኑ እናንተን ደግሞ ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው እንደ ሆኑ ቃላችሁን ደግሞ ይጠብቃሉ።


ወንድሞቹ ስንኳ አላመኑበትም ነበርና።


እንኪያስ እውነቱን ስለ ነገርኋችሁ ጠላት ሆንሁባችሁን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos