ዘኍል 11:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ ሁሉ በየድንኳኖቻቸው ደጃፍ ላይ በየቤተሰባቸው ቆመው ሲያለቅሱ ሙሴ ሰማቸው፤ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ተቈጥቶ ስለ ነበረ ሙሴ በጣም ተጨነቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ፣ ሕዝቡ ሁሉ በየቤተ ሰቡ፣ በየድንኳኑ ደጃፍ ሆኖ ሲያለቅስ ሰማ። እግዚአብሔርም እጅግ ተቈጣ፤ ሙሴም ተጨነቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ሕዝቡ በየወገኑ፥ ሰው ሁሉ በየድንኳኑ ደጃፍ፥ ሲያለቅሱ ሰማ፤ የጌታም ቁጣ እጅግ ነደደ፤ ሙሴም በጣም ቅር ተሰኘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እያንዳንዳቸው በየወገናቸው በድንኳኑ ደጃፍ፥ ሲያለቅሱ ሰማ፤ እግዚአብሔርም እጅግ ተቈጣ፤ ነገሩም በሙሴ ፊት ክፉ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ሕዝቡ በወገኖቻቸው፥ ሰው ሁሉ በድንኳኑ ደጃፍ፥ ሲያለቅሱ ሰማ፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ እጅግ ነደደ፤ ሙሴም ተቈጣ። |
እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ በጣም ተቈጥቶአል፤ በኀያልነቱም ይቀጣቸዋል፤ ተራራዎች ይናወጣሉ፤ የሞቱ ሰዎችም አስከሬን እንደ ጥራጊ በየመንገዱ ዳር ይወድቃል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ አይበርድም፤ እንደገናም ሊቀጣቸው ተዘጋጅቶአል።
ቊጣዬ እንደ እሳት እንዲቀጣጠል ስላደረጋችሁ እርሱም ለዘለዓለም ስለሚነድ የሰጠኋችሁን ርስት ሁሉ እንድታጡና በማታውቁት አገር ጠላቶቻችሁን እንድታገለግሉ አደርጋለሁ።”
እስራኤላውያን ስለ ደረሰባቸው ችግር ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ማጒረምረም ጀመሩ፤ እግዚአብሔርም የማጒረምረም ጩኸታቸውን ሰምቶ እጅግ በመቈጣት የሚባላ እሳት ላከባቸው፤ ያም እሳት ከሰፈሩ አንዱን ክፍል አወደመ።
እግዚአብሔርንም እንዲህ አለው፦ “ይህን ከባድ ነገር በእኔ በአገልጋይህ ላይ ስለምን አመጣህብኝ? ለምንስ በፊትህ ሞገስን አላገኘሁም? የዚህን ሁሉ ሕዝብስ ከባድ ኀላፊነት ለምን በእኔ ላይ ጫንከው?
ስለዚህ ሕዝቡ ከቆሬ፥ ከዳታንና ከአቤሮን ድንኳኖች ፈቀቅ አሉ። ዳታንና አቤሮንም ወጥተው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በድንኳናቸው ደጃፍ ቆመው ነበር።
በእግዚአብሔርና በሙሴም ላይ ክፉ ቃል በመናገር እንዲህ ሲሉ አጒረመረሙ፤ “ምግብና ውሃ በሌለበት በዚህ በረሓ እንሞት ዘንድ ከግብጽ ምድር ለምን አወጣችሁን? ይህን አስከፊ ምግብ ሰውነታችን ተጸይፎታል!”
ኢየሱስም ይህን በማየት ተቈጥቶ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ስለ ሆነች ሕፃናት ወደ እኔ ይምጡ፤ ተዉ፤ አትከልክሉአቸው፤
ኢየሱስም ስለ ልባቸው ድንዛዜ አዝኖ በዙሪያው ያሉትን በቊጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ” አለው። እርሱም በዘረጋ ጊዜ እጁ ዳነለት።
በቊጣዬ እሳት ይቀጣጠላል፤ እስከ ሲኦል ጥልቀት ድረስ ይነዳል፤ ምድርንና ምርቱን ይበላል። ቃጠሎውም እስከ ተራራዎች መሠረት ድረስ ያቃጥላል።