በይሁዳ ከተሞች ሰዎችም ሕዝብም ሁሉ ከቀንድ ከብቶቻቸውና ከበጎቻቸው ዐሥራት አውጥተው ሰጡ፤ እንዲሁም ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር የተለየ ያደረጉትን ስጦታ አምጥተው ከመሩት፤
ነህምያ 10:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰበሰብነው መከር የመጀመሪያውን እህል ዱቄት ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን እንሰጣለን፤ ሌላውንም የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይትና የመሳሰለውንም ፍራ ፍሬ ሁሉ የመጀመሪያውን መባ አድርገን እናቀርባለን። ከእርሻ መንደሮቻችን ግብር ለሚሰበስቡት ሌዋውያንም ምድራችን ከምታበቅለው የእህል መከር ዐሥራት እያወጣን እንሰጣለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዚህም በላይ የቡሖአችንን፣ የእህል ቍርባናችንን፣ የዛፎቻችንን ፍሬ ሁሉ፣ አዲሱን የወይን ጠጃችንንና የዘይታችንን በኵራት ወደ ካህናቱ፣ ወደ አምላካችን ቤት ዕቃ ቤቶች እናመጣለን። እኛ በምንሠራባቸው ከተሞች ሁሉ ያለውን ዐሥራት የሚሰበስቡት ሌዋውያን ስለ ሆኑ፣ የሰብላችንን ዐሥራት ወደ ሌዋውያኑ እናመጣለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእህላችንንም በኵራት፥ የእጅ ማንሣታችንን ቁርባን፥ የዛፍ ሁሉ ፍሬ፥ ወይኑንና ዘይቱንም ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ አሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን አሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእህላችንንም ቀዳምያት፥ የዛፉን ሁሉ ፍሬ፥ የወይኑንና የዘይቱንም ፍሬ ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ ዐሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን ዐሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን። |
በይሁዳ ከተሞች ሰዎችም ሕዝብም ሁሉ ከቀንድ ከብቶቻቸውና ከበጎቻቸው ዐሥራት አውጥተው ሰጡ፤ እንዲሁም ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር የተለየ ያደረጉትን ስጦታ አምጥተው ከመሩት፤
እንዲሁም አገልግሎቱን የሚፈጽሙት የቤተ መቅደሱ መዘምራንና ሌሎችም ሌዋውያን ኢየሩሳሌምን ለቀው በመውጣት ወደየእርሻቸው ተመልሰው መግባታቸውን ተገነዘብኩ፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ሕዝቡ ለመዘምራኑና ለሌዋውያኑ በቂ መተዳደሪያ ባለመስጠታቸው ነበር።
ከዚህም በኋላ እስራኤላውያን ሁሉ እንደገና ከእህልና ከወይን ጠጅ፥ ከወይራ ዘይትም የሚፈለግባቸውን ከዐሥር አንድ እያወጡ ወደ ቤተ መቅደስ ዕቃ ግምጃ ቤት ማምጣት ጀመሩ።
ከዚህም የተነሣ የእህል መባ፥ ዕጣን፥ የቤተ መቅደስ ንዋያተ ቅድሳት፥ ከእህል፥ ከወይን ጠጅ፥ ከወይራ ዘይት ተውጣጥቶ ለሌዋውያኑ ለቤተ መቅደስ መዘምራንና ለዘብ ጠባቂዎች የሚሰጠው ዐሥራትና ለካህናቱ የሚሰጥ መባ ሁሉ እንዲቀመጥበት ታስቦ በተለይ የተሠራውን ታላቅ ክፍል ጦቢያ በመኖሪያነት ይጠቀምበት ዘንድ ኤልያሺብ ፈቅዶለት ነበር።
ክፍሎቹም በሕጉ መሠረት በሥርዓት እንዲነጹና የቤተ መቅደሱም ንዋያተ ቅድሳት፥ የእህል መባውና ዕጣኑ ወደዚያ ተመልሰው እንዲገቡ ትእዛዝ ሰጠሁ።
“ከእስራኤል ሕዝብም ሆነ ከእንስሶቹ በኲር ሆኖ የተወለደ ሁሉ ለእኔ መሆን ይገባዋል፤ ስለዚህ በኲር ሆኖ የተወለደውን ሁሉ ለእኔ እንዲሆን ቀድሰው።”
እያንዳንዱ ቤተሰብ ሁለት እንጀራ በመወዝወዝ ልዩ መባ አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ እያንዳንዱ እንጀራ እርሾ ገብቶበት ከሁለት ኪሎ የላመ ዱቄት ጋር ተጋግሮ ስለሚሰበሰበው አዲስ መከር ለእግዚአብሔር የበኲራት መባ ሆኖ ይቅረብ።
በቤተ መቅደሴ ሲሳይ ይበዛ ዘንድ ዐሥራቴን በሙሉ ወደ ጐተራ አግቡ፤ እናንተ ይህን ብታደርጉ እኔ ደግሞ የሰማይን መስኮቶች ከፍቼ መልካም የሆነውን በረከት ሁሉ አብዝቼ ባልሰጣችሁ በዚህ ልትፈትኑኝ ትችላላችሁ።
ሰው የእግዚአብሔርን ሀብት ይዘርፋልን? ሆኖም እናንተ እኔን ዘርፋችኋል፥ እናንተ ግን እንዴት ከአንተ እንዘርፋለን ብላችሁ ትጠይቃላችሁ፤ ከእኔ የዘረፋችሁት ዐሥራትንና መባን ባለመክፈላችሁ ነው።
“እስራኤላውያን ለእኔ የሚያቀርቡት የሰውም ሆነ የእንስሳ በኲር ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን የበኲር ልጅ ለመዋጀት ዋጋውን በጥሬ ገንዘብ መቀበል አለባችሁ፤ እንዲሁም ንጹሕ ስላልሆነው የእንስሳ በኲር ምትክ ዋጋውን በጥሬ ገንዘብ መቀበል ትችላላችሁ፤
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል ሕዝብ ለእኔ የሚያመጡትን ዐሥራት ሁሉ የሌዋውያን ድርሻ እንዲሆን ሰጥቻቸዋለሁ፤ ይህም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚሰጡት አገልግሎት ደመወዝ ይሆንላቸዋል።
ከአንድ ዐይነት ሊጥ የመጀመሪያው ክፍል የተቀደሰ ከሆነ ሊጡ በሙሉ የተቀደሰ ይሆናል፤ እንዲሁም የአንድ ዛፍ ሥሩ የተቀደሰ ከሆነ ቅርንጫፎቹም የተቀደሱ ይሆናሉ።