ማቴዎስ 9:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ “ስለምን ይህን ክፉ ነገር በልባችሁ ታስባላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ሐሳባቸውን ተረድቶ እንዲህ አለ፤ “ክፉ ነገር በልባችሁ ለምን ታስባላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ ግን ሐሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ “ስለምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ “ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ፦ ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ? |
ኢየሱስም ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ “አንድ መንግሥት ተከፋፍሎ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ከሆነ፥ ያ መንግሥት ይወድቃል። እንዲሁም አንድ ከተማ ወይም አንድ ቤተሰብ እርስ በርሱ ከተለያየ ጸንቶ መኖር አይችልም።
ኢየሱስ ግን ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ “አንድ መንግሥት ተከፋፍሎ እርስ በርስ የሚለያይ ከሆነ፥ ያ መንግሥት ይጠፋል፤ እንዲሁም አንድ ቤተሰብ እርስ በርሱ ከተለያየ ይወድቃል።
ኢየሱስም ሊጠይቁት እንደ ፈለጉ ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርሳችሁ የምትጠያየቁ፥ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ደግሞም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁ’ ስላልኳችሁ ነውን?
አንተ ሁሉን እንደምታውቅና ማንም ጥያቄ ሊያቀርብልህ እንደማያስፈልግህ አሁን ዐወቅን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ወጣህ እናምናለን።”
ሦስተኛ ጊዜም “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ትወደኛለህን?” አለው። ሦስተኛ ጊዜ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና “ጌታ ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፥ እኔ እንደምወድህም ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “በጎቼን አሰማራ፤
ነገር ግን ከእናንተ መካከል አንዳንዶች የማያምኑ አሉ፤” ኢየሱስ ይህን የተናገረው ከመጀመሪያ አንሥቶ የማያምኑ እነማን እንደ ነበሩና አሳልፎ የሚሰጠውም ማን እንደ ሆነ ያውቅ ስለ ነበር ነው።
በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “የእግዚአብሔርን መንፈስ ለመፈታተን እንዴት ተስማማችሁ? እነሆ! ባልሽን ቀብረው የሚመለሱት ሰዎች በበር ናቸው፤ አንቺንም ወስደው ይቀብሩሻል” አላት።
ልጆችዋንም በሞት እቀጣለሁ፤ አብያተ ክርስቲያንም ሁሉ የሰውን ሐሳብና ምኞት የምመረምር እኔ መሆኔን ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደየሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።