Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 139:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አንተ ስቀመጥም ሆነ ስነሣ ታውቃለህ፤ ሐሳቤን ሁሉ ከሩቅ ሆነህ ታስተውላለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ፤ የልቤንም ሐሳብ ገና ከሩቁ ታስተውላለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አወቅህ፥ ሐሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሁል​ጊዜ በል​ባ​ቸው ዐመ​ፃን የሚ​መ​ክሩ፥ ይገ​ድ​ሉኝ ዘንድ ይከ​ብ​ቡ​ኛል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 139:2
17 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስም ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ “ስለምን ይህን ክፉ ነገር በልባችሁ ታስባላችሁ?


እኔ ግን መነሣትህንና መቀመጥህን፥ መውጣትህንና መግባትህን፥ እንዲሁም እኔን መቃወምህን ዐውቃለሁ።


ኢየሱስ ግን የልባቸውን ሐሳብ ዐውቆ አንድ ሕፃን ልጅ አመጣና በአጠገቡ አቆመው፤


እግዚአብሔር የሰዎችን ሁሉ ሐሳብና፥ ከንቱነታቸውን ያውቃል።


“እኔ ስለ አንተ ሁሉን ነገር ዐውቃለሁ፤ ምን እንደምታደርግና ወዴት እንደምትሄድ እመለከታለሁ፤ በእኔ ላይ በቊጣ መነሣሣትህንም ተረድቼአለሁ።


እግዚአብሔር በየቦታው የሚደረገውን ነገር ሁሉ ያያል። መልካምም ሆነ ክፉ ድርጊትን ይመለከታል።


ትንሽ ነገር የሚደረግበትን ቀን የናቀ ቱምቢውን በዘሩባቤል እጅ ሲያይ ይደሰታል፤ እነዚህ ሰባቱ መቅረዞች ዓለምን የሚያካልሉ የእግዚአብሔር ዐይኖች ናቸው።”


የመንከራተት ቀኖቼን ቈጥረሃል፤ እንባዎቼንም በጠርሙስ ውስጥ አስቀምጠሃል፤ እያንዳንዳቸውንም መዝግበሃል።


ከእነርሱም አንዱ “ንጉሥ ሆይ፥ ከእኛ መካከል ይህን የሚያደርግ ማንም የለም፤ በመኝታ ክፍልህ እንኳ ሆነህ የምትናገረውን ሁሉ ሳይቀር ለእስራኤል ንጉሥ ምሥጢሩን የሚገልጥለት ኤልሳዕ የተባለው ነቢይ ነው” ሲል መለሰለት።


አጋርም “በእርግጥ የሚያየኝን እግዚአብሔርን በዐይኔ አይቼ በሕይወት ኖርሁን?” በማለት ያነጋገራትን ጌታ “ኤልሮኢ” አለችው፤ ትርጒሙም “የሚያየኝ አምላክ” ማለት ነው።


ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አንተን እንደማመጣ አገልጋዮቼ የእስራኤል ነቢያት በቀድሞ ዘመን በመደጋገም ትንቢት ተናግረዋል።”


ብዙ ከባድ ችግሮች ሲደርሱባቸው ይህ በልጆቻቸው የማይረሳ መዝሙር ሲዘመር ምስክር ይሆንባቸዋል። በመሐላ ቃል ወደገባሁላቸው ምድር ከማስገባቴ በፊት አሁን እንኳ ምን ዐይነት ዝንባሌ እንዳላቸው ዐውቃለሁ።”


ነገር ግን ስለ አንተ በየቀኑ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎችም ተቈጥረናል።


ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ወረደ፤ እንዲህም አለኝ፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ተናገር፦ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ይህን ነገር ተናግራችኋል፤ እኔም በሐሳባችሁ ያለውን ነገር ዐውቃለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios