ማቴዎስ 8:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም “ቀበሮዎች ጒድጓድ አላቸው፤ በአየር ላይ የሚበሩ ወፎችም የሚሰፍሩበት ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት ስፍራ የለውም” ሲል መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም፣ “ቀበሮዎች ጕድጓድ፣ የሰማይ ወፎችም ጐጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት ቦታ የለውም” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም “ቀበሮዎች ጉድጓድ፥ የሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት የለውም፤” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም “ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፤ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም፤” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም፦ ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው። |
ንጉሤና አምላኬ የሠራዊት ጌታ ሆይ! ድንቢጦች ለመኖሪያቸው ጎጆ ሠርተዋል፤ ዋኖሶችም ጫጩቶቻቸውን የሚያኖሩበት በመሠዊያዎችህ አጠገብ ቤት አላቸው።
በሰው ልጅ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ሁሉ በደሉ ይቅር ይባልለታል። በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ሁሉ ግን በዚህ ዓለምም ሆነ በሚመጣው ዓለም በደሉ ይቅር አይባልለትም።
ዮናስ በዓሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንዳሳለፈ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በመቃብር ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ያሳልፋል።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ የሰው ልጅ በክብር ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት በአዲሱ ዓለም የእኔ ተከታዮች የሆናችሁ፥ እናንተም፥ በዐሥራ ሁለት ዙፋኑ ላይ ትቀመጣላችሁ፤ በዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ነገዶች ላይ ትፈርዳላችሁ።
በዚህ በከሐዲና በኃጢአተኛ ትውልድ ፊት በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ እኔም የሰው ልጅ በአባቴ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር ስመጣ በእርሱ አፍርበታለሁ።”
በዚያም የበኲር ልጅዋን ወለደች፤ በመታቀፊያ ጨርቅ ጠቀለለችው፤ በእንግዶች ማደሪያ ስፍራ ስላላገኙ በበረት በከብቶች መመገቢያ ግርግም ውስጥ አስተኛችው።
የሄሮድስ ቤት አዛዥ የነበረው የኩዛ ሚስት ዮሐና፥ ሶስናና ሌሎችም ብዙዎች ነበሩ፤ እነዚህ ሴቶች ኢየሱስንና ደቀ መዛሙርቱን በገንዘባቸው ያገለግሉ ነበር።
ኢየሱስም “ቀበሮዎች ጒድጓድ አላቸው፤ የሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ አስጠግቶ የሚያሳርፍበት ስፍራ የለውም፤” ሲል መለሰለት።
ሰዎቹም “በሕግ ተጽፎ የምናገኘው ‘መሲሕ ለዘለዓለም ይኖራል’ የሚል ነው፤ ታዲያ፥ አንተ፥ ‘የሰው ልጅ ወደ ላይ ከፍ ማለት አለበት’ እንዴት ትላለህ? ይህስ የሰው ልጅ ማን ነው?” አሉት።
ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ።”
እናንተ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁ፤ እርሱ ምንም እንኳ ሀብታም ቢሆን በእርሱ ድኻ መሆን እናንተ ሀብታሞች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ብሎ ድኻ ሆነ።