ማቴዎስ 4:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም መልሶ “ ‘ጌታ አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም፣ “እንደዚሁም በመጻሕፍት፣ ‘ጌታ አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሎ ተጽፏል” ብሎ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም “‘ጌታ አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም “ ‘ጌታን አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም፦ ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው። |
ስለዚህም “የምንጠጣው ውሃ ስጠን” ብለው በሙሴ ላይ አጒረመረሙ። ሙሴም “ስለምን ትወቅሱኛላችሁ? ስለምንስ እግዚአብሔርን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።
እስራኤላውያን “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?” በማለት በማጒረምረማቸውና እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያ ስፍራ ማሳህና እና መሪባ ተብሎ ተጠራ።
እንደምናየው ከሆነ እነሆ፥ ክፉ አድራጊዎች ዕድለኞች ናቸው፤ በእርግጥም እነርሱ በብልጽግና ይኖራሉ፤ እግዚአብሔርን እንኳ እየተፈታተኑት ምንም ችግር አይደርስባቸውም እያላችሁ ትናገራላችሁ።’ ”
ከእነዚህ ሕዝብ አንዱም ወደዚያች ምድር ለመግባት በሕይወት አይኖርም፤ በግብጽ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግኋቸውን ተአምራት ሁሉ አይተዋል፤ ነገር ግን የትዕግሥቴን ብዛት ደጋግመው በመፈታተን ለእኔ መታዘዝ እምቢ አሉ።
ስለዚህ ኢየሱስን “እነዚህ ሕፃናት የሚሉትን ትሰማለህን?” አሉት፤ እርሱም “አዎ፥ እሰማለሁ፤ ‘ከልጆችና ከሚጠቡት ሕፃናት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ’ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው፤
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “በቅዱሳት መጻሕፍት ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ ዋና የማእዘን ራስ ሆነ፤ ይህም የጌታ ሥራ ነው፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’ ተብሎ የተጻፈውን ከቶ አላነበባችሁምን?
በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “የእግዚአብሔርን መንፈስ ለመፈታተን እንዴት ተስማማችሁ? እነሆ! ባልሽን ቀብረው የሚመለሱት ሰዎች በበር ናቸው፤ አንቺንም ወስደው ይቀብሩሻል” አላት።