Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሚልክያስ 3:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እንደምናየው ከሆነ እነሆ፥ ክፉ አድራጊዎች ዕድለኞች ናቸው፤ በእርግጥም እነርሱ በብልጽግና ይኖራሉ፤ እግዚአብሔርን እንኳ እየተፈታተኑት ምንም ችግር አይደርስባቸውም እያላችሁ ትናገራላችሁ።’ ”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አሁን ግን ትዕቢተኞችን ቡሩካን እንላቸዋለን፤ ክፉ አድራጊዎች ይበለጽጋሉ፤ እግዚአብሔርን የሚፈታተኑትም ያመልጣሉ።’ ”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አሁንም ትዕቢተኞችን የተባረኩ ብለን እንጠራቸዋለን፤ ክፉንም የሚሠሩ ታንጸዋል፥ እግዚአብሔርንም ይፈታተናሉ፥ ያመልጣሉም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አሁንም የሚታበዩትን ሰዎች ብፁዓን ብለን እንጠራቸዋለን፣ ክፉንም የሚሠሩ ጸንተዋል እግዚአብሔርንም ይፈታተናሉ፥ ያመልጣሉም ብላችኋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አሁንም የሚታበዩትን ሰዎች ብፁዓን ብለን እንጠራቸዋለን፥ ክፉንም የሚሠሩ ጸንተዋል እግዚአብሔርንም ይፈታተናሉ፥ ያመልጣሉም ብላችኋል።

Ver Capítulo Copiar




ሚልክያስ 3:15
37 Referencias Cruzadas  

ሆኖም እንደምንም ራሱን ተቈጣጥሮ በመታገሥ ወደ ቤቱ ደረሰ፤ ከዚህ በኋላ ወዳጆቹን ወደ ቤቱ ጠርቶ ሚስቱ ዜሬሽም አብራ እንድትገኝ አደረገ።


ኢዮብ ምንም እንኳ ይህ ሁሉ ፈተና ቢደርስበት ከቶ ኃጢአት አልሠራም፤ በእግዚአብሔርም ላይ አላማረረም።


ኀይላቸውን እንደ አምላክ አድርገው የሚቈጥሩ ሌቦችና እግዚአብሔርን የካዱ ሰዎች እንኳ በሰላም ይኖራሉ።


እነዚያ ‘ክፉ ሰዎች መቅሠፍት በሚመጣበት ጊዜ ጒዳት አይደርስባቸውም፤ የእግዚአብሔር ቊጣም ሲገለጥ ያመልጣሉ’ ሲሉ ተናግረዋል።


ራስህን ሁሉን ወደሚችል አምላክ ብትመልስ እንደ ቀድሞህ ትሆናለህ። ከቤትህ የክፋትን ሥራ አስወግድ


ኃጢአተኛ በክፉ ምኞቱ ይመካል፤ ጌታ ሆይ! እነዚህ ስግብግብ ሰዎች ይጠሉሃል፤ ይሰድቡህማል።


በበረሓ ሳሉ ብዙ ነገር ተመኙ፤ እግዚአብሔርንም ተፈታተኑት።


ስሕተት ለማድረግ ከመመኘትና ከክፉ አድራጊዎች ጋር በክፉ ሥራ ከመተባበር ጠብቀኝ፤ የበዓላቸው ግብዣ ተካፋይ ከመሆን ጠብቀኝ።


ሰው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ቢደሰትና ሁሉም ነገር ስለ ተሳካለት ቢመሰገንም እንኳ


አይደለም! በልባችሁ ክፉ ነገርን ታቅዳላችሁ፤ በምድር ላይ የምትፈጽሙትም ሁሉ የዐመፅ ሥራ ነው።


እንግዲህ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው፤ ሁልጊዜ እንደ ተዝናኑ ናቸው። ዘወትርም ተጨማሪ ሀብት ያገኛሉ።


ይህም የሆነው ትዕቢተኞችና ክፉዎች ሰዎች ሲበለጽጉ በማየቴ ቅናት አድሮብኝ ነው።


የተመኙትን ምግብ በመጠየቅ ሆን ብለው እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።


በመደጋገም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት፤ የእስራኤልንም ቅዱስ አሳዘኑት።


የእርሱ ሕዝቦች ግን በልዑል እግዚአብሔር ላይ ዐመፁ፤ ተፈታተኑትም፤ ትእዛዞቹንም አልፈጸሙም።


እነርሱ ያደረግኹላቸውን ድንቅ ነገር ቢያዩም እንኳ በዚያ ተፈታተኑኝ፤ ተገዳደሩኝም።


የክፉ ሰዎች ምኞት ዘወትር ክፉ ነገርን ለማድረግ ነው፤ ደጋግ ሰዎች ግን እንደ መልካም ተክል መልካም ፍሬን ያፈራሉ።


በምድር ላይ የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፤ አንዳንድ ጊዜ ደጋግ ሰዎች ለክፉ ሰዎች የሚገባውን ቅጣት ይቀበላሉ፤ ክፉ ሰዎች ደግሞ ለደጋግ ሰዎች የሚገባውን ዋጋ ያገኛሉ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ነው አልኩ።


እንግዲህ ትንፋሹ አፍንጫው ላይ በሆነች በሟች ሰው መተማመናችሁ ይቅር፤ እርሱ ለምንም አይጠቅምም።


እኔ የምጠላውን ይህን ሁሉ ነገር ከፈጸማችሁ በኋላ ወደ ቤተ መቅደሴ መጥታችሁ በፊቴ በመቆም ‘እኛ ከጥፋት ድነናል!’ ትላላችሁ።


ንጉሡም እንዲህ አለ፦ “ይህችን ታላቋን ባቢሎን የነገሥታት መኖሪያና ዋና ከተማ ሆና የእኔ ክብርና ግርማ እንዲገለጥባት በሥልጣኔ የሠራኋት እኔ አይደለሁምን?”


“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”


ስለዚህ ዳንኤል ተይዞ መጥቶ ወደ አንበሶች ጒድጓድ እንዲጣል ንጉሡ አዘዘ፤ ዳንኤልንም “ሁልጊዜ በታማኝነት የምታገለግለው አምላክህ ያድንህ” አለው።


በቃላችሁ እግዚአብሔርን አሰልችታችሁታል፤ “እርሱን ያሰለቸነው በምንድን ነው?” ትላላችሁ፤ እርሱን ያሰለቻችሁት፦ “ክፉ አድራጊ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፤ እግዚአብሔርንም ያስደስተዋል” በማለት ወይም “የፍትሕ አምላክ የት አለ?” ብላችሁ በመጠየቅ ነው።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።


በተቀጠረው ቀን ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለበሰና በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ለሕዝቡ ንግግር አደረገ።


በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “የእግዚአብሔርን መንፈስ ለመፈታተን እንዴት ተስማማችሁ? እነሆ! ባልሽን ቀብረው የሚመለሱት ሰዎች በበር ናቸው፤ አንቺንም ወስደው ይቀብሩሻል” አላት።


ከእነርሱ አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑትና በእባብ ተነድፈው እንደ ሞቱ እኛም ጌታን አንፈታተነው።


እዚያ አባቶቻችሁ ተፈታተኑኝ፤ ተገዳደሩኝም፤ አርባ ዓመት ያደረግኹትንም አዩ” ይላል እግዚአብሔር።


እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos