18 የተመኙትን ምግብ በመጠየቅ ሆን ብለው እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።
18 እጅግ የተመኙትን ምግብ በመጠየቅ፣ እግዚአብሔርን በልባቸው ተፈታተኑት።
18 የተመኙትን መብል እየጠየቁ፥ እግዚአብሔርን በልባቸው ፈተኑት።
“ ‘ማሳህ’ ተብሎ በሚጠራው ቦታ እንዳደረጋችሁት ዐይነት እግዚአብሔር አምላካችሁን አትፈታተኑ፤
ከእስራኤላውያን ጋር የሚጓዙ የውጪ አገር ሰዎች ሥጋ ለመብላት የነበራቸው ፍላጎት ከፍተኛ ነበር፤ እስራኤላውያንም እንዲህ እያሉ ማልቀስ ጀመሩ፦ “የምንበላውን ሥጋ ከየት እናገኛለን!
ከእነርሱ አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑትና በእባብ ተነድፈው እንደ ሞቱ እኛም ጌታን አንፈታተነው።
እነርሱ ክፉ ነገር እንደ ተመኙ እኛም ክፉ ነገር እንዳንመኝ ይህ ሁሉ ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ሆኖናል።
እነርሱ ያደረግኹላቸውን ድንቅ ነገር ቢያዩም እንኳ በዚያ ተፈታተኑኝ፤ ተገዳደሩኝም።
ስለዚህም “የምንጠጣው ውሃ ስጠን” ብለው በሙሴ ላይ አጒረመረሙ። ሙሴም “ስለምን ትወቅሱኛላችሁ? ስለምንስ እግዚአብሔርን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።
እስራኤላውያን “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?” በማለት በማጒረምረማቸውና እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያ ስፍራ ማሳህና እና መሪባ ተብሎ ተጠራ።