ሉቃስ 24:50 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከኢየሩሳሌም ከተማ አውጥቶ እስከ ቢታንያ ወሰዳቸው፤ በዚያም እጆቹን ዘርግቶ ባረካቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ እስከ ቢታንያ ይዟቸው ወጣ፤ እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስከ ቢታንያም ወሰዳቸው፤ እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስከ ቢታንያም ወደ ውጭ አወጣቸው፤ እጁንም አንሥቶ በላያቸውም ጭኖ ባረካቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። |
ዮሴፍም “እነዚህ እግዚአብሔር በዚህ አገር ሳለሁ የሰጠኝ የእኔ ልጆች ናቸው” ብሎ ለአባቱ መለሰለት። ያዕቆብም “እባርካቸው ዘንድ ወደ እኔ አቅርብልኝ” አለው።
እንግዲህ እነዚህ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው፤ አባታቸው በባረካቸው ጊዜ ለእያንዳንዱ ተስማሚ የሆነውን የበረከት ቃል የተናገረው በዚህ ሁኔታ ነበር።
ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም በቀረቡ ጊዜ በቤተ ፋጌና በቢታንያ አድርገው ወደ ደብረ ዘይት ደረሱ፤ ከዚያም ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፦
ከዚህ በኋላ ደብረ ዘይት ከተባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ የደብረ ዘይት ተራራ ከኢየሩሳሌም የሚርቀው የሰንበት መንገድ (አንድ ኪሎ ሜትር) ያኽል ነው።