Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 24:50 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

50 ከዚህ በኋላ እስከ ቢታንያ ይዟቸው ወጣ፤ እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

50 እስከ ቢታንያም ወሰዳቸው፤ እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

50 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከኢየሩሳሌም ከተማ አውጥቶ እስከ ቢታንያ ወሰዳቸው፤ በዚያም እጆቹን ዘርግቶ ባረካቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

50 እስከ ቢታ​ን​ያም ወደ ውጭ አወ​ጣ​ቸው፤ እጁ​ንም አን​ሥቶ በላ​ያ​ቸ​ውም ጭኖ ባረ​ካ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

50 እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 24:50
15 Referencias Cruzadas  

ከዚያም ደብረ ዘይት ከተባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ይህም ተራራ ከኢየሩሳሌም የሰንበት መንገድ ያህል ይርቅ ነበር።


ትቷቸው ከከተማው ወጣ፤ ወደ ቢታንያም ሄዶ በዚያው ዐደረ።


እነዚህ ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው። ይህም እያንዳንዳቸውን ተገቢ በሆነው በረከት አባታቸው ሲባርካቸው የተናገረው ቃል ነው።


ወደ ኢየሩሳሌም በደብረ ዘይት ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፣ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ በማለት ላካቸው፤


ሕፃናቱንም ዐቀፋቸው፤ እጁንም ጭኖ ባረካቸው።


ዮሴፍም፣ “እነዚህ እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ብሎ ለአባቱ መለሰለት። እስራኤልም፣ “አቅርባቸውና ልመርቃቸው” አለ።


ከመሞቴ በፊት እንድመርቅህ የምወድደውን ዐይነት ጣዕም ያለው ምግብ አዘጋጅተህ አብላኝ።”


አሮንም እጆቹን ወደ ሕዝቡ ዘርግቶ ባረካቸው፤ የኀጢአት መሥዋዕቱን፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረቱን መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ ወረደ።


ከዚያም ኢያሱ መርቆ አሰናበታቸው፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ተመለሱ።


እየባረካቸውም ሳለ፣ ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ሰማይ ዐረገ።


ይህን ካለ በኋላ እያዩት ወደ ላይ ዐረገ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰወረችው።


እንግዲህ ወንዶች በሁሉም ቦታ ያለ ቍጣና ያለ ክርክር የተቀደሱ እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሣት እንዲጸልዩ እፈልጋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios