ሉቃስ 10:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ተፈላጊው አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያም የሚሻለውን ነገር መርጣለች፤ እርሱንም ከእርስዋ የሚወስድባት ማንም የለም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያም እኮ መልካሙን ድርሻ መርጣለች፤ ይህም ከርሷ አይወሰድም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያምም መልካሙን ድርሻ መርጣለች፤ ከእርሷም አይወሰድባትም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥቂት ይበቃል፤ ያም ባይሆን አንድ ይበቃል፤ ማርያምስ የማይቀሙአትን መልካም ዕድል መረጠች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት። |
እግዚአብሔርን አንድ ነገር እለምነዋለሁ፤ የምለምነውም፦ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ የእግዚአብሔርን አስደናቂነት እንድመለከትና በቤተ መቅደሱም መጸለይ እንድችል ነው።
አንድ ቀን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ ጸሎቱንም ባበቃ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ! ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት እንዳስተማራቸው፥ አንተም እኛን መጸለይ አስተምረን!” አለው።
ያላችሁን ሁሉ ሸጣችሁ ገንዘቡን ለድኾች ስጡ፤ የማያረጅ የገንዘብ ቦርሳም አዘጋጅታችሁ ገንዘባችሁን ሌባ በማይደርስበት፥ ብል በማይበላበትና ከቶም በማያልቅበት ቦታ በመንግሥተ ሰማያት አስቀምጡ።
ሀብታሙም ሰው መጋቢውን አስጠርቶ ‘ይህ የምሰማብህ ነገር ምንድን ነው? ከእንግዲህ ወዲህ መጋቢዬ ልትሆን አትችልምና በመጋቢነትህ የሠራህበትን የንብረቴን ሒሳብ አቅርብልኝ’ አለው።
“አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በምድራዊ ሕይወትህ ዘመን ብዙ መልካም ነገር አግኝተህ እንደ ተደሰትህ አስታውስ፤ አልዓዛር ግን በችግር ላይ ነበር፤ ስለዚህ አሁን እርሱ እዚህ ሲደሰት አንተ ትሠቃያለህ።
ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ ሰውየውን፥ “እንግዲያውስ ገና አንድ ነገር ማድረግ ይቀርሃል፤ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ገንዘቡን ለድኾች ስጥ፤ በሰማይ የተከማቸ ሀብት ታገኛለህ፤ ከዚያም በኋላ መጥተህ ተከተለኝ” አለው።
በዚያን ጊዜ ማርያም ዋጋው እጅግ የከበረ ከንጹሕ ናርዶስ የተሠራ፥ ግማሽ ሊትር የሚሆን አንድ ብልቃጥ ሽቶ ወስዳ፥ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ በጠጒርዋም አበሰቻቸው፤ ቤቱም በሽቶው መዓዛ ተሞላ።
እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ለዘለዓለም ከቶ አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ፥ ለሚጠጣው ሰው ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል።”
“እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማና በላከኝም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ እርሱ ከሞት ወደ ሕይወት የተሻገረ ስለ ሆነ አይፈረድበትም።
ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ።”
እነሆ፥ እኔ በሕይወትና በሞት መካከል፥ በእግዚአብሔር በረከትና መርገም መካከል ምርጫ እሰጣችኋለሁ፤ በምታደርጉትም ምርጫ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ ምስክር አድርጌ እጠራለሁ፤ ስለዚህም እናንተና ዘሮቻችሁ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጡ።
እርሱን ማምለክ መልካም መስሎ ካልታያችሁ ግን የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በነበሩበት ጊዜ ያመልኩአቸው የነበሩትን ወይም አሁን በምድራቸው የምትኖሩባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደሆን የምታመልኩትን ዛሬውኑ ምረጡ፤ እኔና ቤተሰቤ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።”
ኢያሱም “እንግዲህ እግዚአብሔርን ለማምለክ ስለ መምረጣችሁ ራሳችሁ በራሳችሁ ላይ ምስክሮች ናችሁ” ሲል ነገራቸው። እነርሱም “አዎ፤ ምስክሮች ነን፤” አሉ።