ዘሌዋውያን 5:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ባለማወቅ ማናቸውንም ርኩስ ነገር ለምሳሌ የአውሬ፥ የቤት እንስሳ ወይም በደረቱ እየተሳበ የሚንቀሳቀስ ፍጥረት በድን ቢነካ፥ ያደረገውን ስሕተት ካወቀበት ጊዜ አንሥቶ በደል ይሆንበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ማንኛውም ሰው ሳያውቅ በሥርዐቱ መሠረት የተከለከለውን ርኩስ ነገር ቢነካ፣ ይኸውም፦ የረከሰ የአውሬ በድን ወይም የረከሰ የቤት እንስሳ በድን ወይም በደረቱ እየተሳበ የሚንቀሳቀሰውን የረከሰ ፍጥረት በድን ቢነካ ይህ ሰው ረክሷል፤ በደለኛም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም ሰው ማንኛውንም ርኩስ ነገር ማለትም የረከሰ አውሬ በድን፥ ወይም የረከሰ ከብት በድን፥ ወይም በደረቱ እየተሳበ የሚርመሰመስ የረከሰ ፍጥረት በድን ሳይታወቀው ቢነካ፥ እርሱ ርኩስ ይሆናል፤ በደለኛም ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርኩስ ነገርን፥ የሞተውን፥ አውሬ የነከሰውን፥ ወይም የበከተ፥ ወይም የሚንቀሳቀስ የእንስሳን በድን የነካ፥ ከእርሱም ያነሣ ሰው ቢኖር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማናቸውም ሰው ሳይታወቀው ርኩስ ነገር ቢነካ፥ የረከሰም አውሬ በድን፥ ወይም የረከሰ ከብት በድን፥ ወይም የረከሰ የተንቀሳቀሰ እንስሳ በድን ቢሆን፥ እርሱም ርኩስ ቢሆን ነገሩ በታወቀው ጊዜ በደል ይሆንበታል፤ |
እናንተ የቤተ መቅደስን ንዋያተ ቅድሳት የተሸከማችሁ! ከባቢሎን ውጡ፤ ከእርሱም ተለዩ፤ ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋም ወጥታችሁ ራሳችሁን አንጹ።
“ባለማወቅ ኃጢአት የሠራው መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ቢሆንና፥ ጉዳዩም ከማኅበረሰቡ ቢሰወር፥ ይህም ኃጢአት እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸው ትእዛዞች አንዱን በማፍረስ በደለኞች ቢያደርጋቸው፥
“አንድ ሰው ባለማወቅ ምንም ዐይነት ይሁን ከሰውነት የሚፈስ አንዳች ርኩስ ነገር ቢነካ፥ ያደረገውን ስሕተት ካወቀበት ጊዜ አንሥቶ በደል ይሆንበታል።
“አንድ ሰው ለክፉም ሆነ ለደግ ስለ ምንም ነገር ያለ ጥንቃቄ በግዴለሽነት ስእለት ቢሳል፥ ያደረገውን ስሕተት ካወቀበት ጊዜ አንሥቶ በደል ይሆንበታል።
ማንም ሰው ንጹሕ ያልሆነው ከሰው ወይም ከእንስሶች የሚወጣ ማንኛውንም ርኩስ ነገር ነክቶ ይህን የአንድነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ ያ ሰው ከእግዚአብሔር ሕዝብ ይለይ። ”
ሐጌም እንደገና “ሬሳ በመዳሰስ የረከሰ አንድ ሰው፥ ከነዚህ የምግብ ዐይነቶች አንዱን ቢነካ፥ ያ የተነካው ምግብ በዕርግጥ ይረክሳልን?” ሲል ጠየቃቸው። ካህናቱም “አዎ፥ ይረክሳል” ሲሉ መለሱለት።
ዐሣማዎችን አትብሉ፤ እነርሱ ሰኮናቸው የተከፈለ ቢሆንም ስለማያመሰኩ የረከሱ ሆነው ይቈጠራሉ፤ እንደነዚህ ያሉትን እንስሶች መብላት ይቅርና በድናቸውን እንኳ አትንኩ።