12 የራሱን ስሕተት የሚያይ ማንም የለም፤ አምላኬ ሆይ! ከተሰወረ በደል አንጻኝ።
12 ስሕተቱን ማን ሊያስተውል ይችላል? ከተሰወረ በደል አንጻኝ።
12 አገልጋይህ ደግሞ ይጠብቀዋል፥ በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል።
“አስተምሩኝ፤ እኔም ዝም እላለሁ፤ ስሕተቴንም አስረዱኝ።
አንተ ስቀመጥም ሆነ ስነሣ ታውቃለህ፤ ሐሳቤን ሁሉ ከሩቅ ሆነህ ታስተውላለህ።
የአንተ ዕውቀት እጅግ ጥልቅ ነው፤ እኔ ላስተውለው ከምችለው በላይ ነው።
ከቊጥር በላይ የሆኑ ችግሮች ያስጨንቁኛል! በደሎቼ ስለ በዙ ማየት አልችልም፤ እነርሱም በቊጥር ከራስ ጠጒሮቼ ይበልጣሉ፤ ስለዚህ ልቤም እየከዳኝ ነው።
በደሌን ሁሉ አጥበህ አስወግድልኝ፤ ከኃጢአቴም አንጻኝ።
ኃጢአት በላያችን በርትቶብን ነበር፤ አንተ ግን በደላችንን ሁሉ ይቅር አልክልን።
ኃጢአታችንን በፊትህ ታኖራለህ፤ የተሰወረውንም በደላችንን ለአንተ በሚታይ ቦታ ታስቀምጣለህ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ ወዳለሁበት ወደ ተራራው ወጥተህ በዚያ ቈይ፤ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችንም እሰጥሃለሁ፤ በእነርሱም ላይ ለሕዝቡ መመሪያዎች ይሆኑ ዘንድ እኔ የጻፍኳቸው ትእዛዞችና ኅጎች ይገኛሉ።”
መልካም ምክርን የሚንቅ ችግር ይደርስበታል፤ ትእዛዝን የሚያከብር ግን ዋጋ ያገኝበታል።
እኛ ሁላችን በኃጢአት ረክሰናል፤ ጽድቃችንም እንደ አደፍ ጨርቅ ሆኖአል፤ ከኃጢአታችን ብዛት የተነሣ ደርቀው በነፋስ እንደሚረግፉ ቅጠሎች ሆነናል።
“የሰው ልብ ከሁሉ ነገር በላይ ተንኰለኛና ጠማማ ነው፤ ውስጠ ምሥጢሩን የሚረዳ ማነው?
እኔ እንደማውቀው ከሆነ ኅሊናዬ አይወቅሰኝም፤ ይህም እኔ ንጹሕ መሆኔን አያስረዳም፤ ነገር ግን በእኔ ላይ የሚፈርድ ጌታ ብቻ ነው።
ሁልጊዜ በዚህ ዐይነት ቢያስቡማ እንዴት መልካም ነበር! ሁልጊዜ ቢያከብሩኝና ትእዛዞቼንም ሁሉ ቢፈጽሙ ሁሉ ነገር ለእነርሱና ለዘሮቻቸው ለዘለዓለም በመልካም ሁኔታ በተከናወነላቸው ነበር።
“ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ ያዘዛችሁን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ሁኑ፤ ከሕግጋቱም አንዱን እንኳ አትጣሱ፤
ወደ ሁለተኛዋ ውስጠኛ ክፍል የሚገባው ግን የካህናቱ አለቃ ብቻ ነው፤ የሚገባውም በዓመት አንድ ቀን ብቻ ነው፤ እርሱም ስለ ራሱ ኃጢአትና ሕዝቡ ባለማወቅ ስላደረገው ኃጢአት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም።
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ እኛም በብርሃን ብንኖር እርስ በርሳችን አንድነት ይኖረናል። ደግሞም የልጁ የኢየሱስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።