Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 19:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ያልነጻ ሰው የሚነካው ነገር ሁሉ የረከሰ ይሆናል፤ ያንንም ዕቃ የሚነካ ሌላ ሰው እስከ ማታ እንደ ረከሰ ይቈያል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የረከሰ ሰው የሚነካው ማንኛውም ነገር ይረክሳል፤ ይህን የነካ ሰው ደግሞ እስከ ማምሻው ድረስ የረከሰ ይሆናል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የረከሰውም ሰው የሚነካው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ የሚነካውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ርኩ​ሱም የሚ​ነ​ካው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆ​ናል፤ የሚ​ነ​ካ​ውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ርኩሱም የሚነካው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ የሚነካውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 19:22
21 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤


ፈሳሽ ያለበት ሰው የተቀመጠበትን ዕቃ ሁሉ የሚነካ እስከ ማታ ድረስ የረከሰ ይሆናል፤ ሰውየው የተቀመጠበትን ማንኛውንም ዕቃ የያዘ ልብሱን አጥቦ፥ ሰውነቱንም ታጥቦ፥ እስከ ማታ ድረስ የረከሰ ይሆናል።


ፈሳሽ ያለበት ሰው እጁን ሳይታጠብ አንድን ሰው ቢነካ ያ ሰው ልብሱን አጥቦ፥ ሰውነቱንም ታጥቦ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


መኝታዋንም የሚነካ ሁሉ ልብሱን ይጠብ፤ ገላውንም ይታጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሁን፤


የምትቀመጥበትን ነገር የሚነካ ሁሉ ልብሱን ይጠብ፤ ገላውንም ይታጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሁን፤


የምትተኛበትን ወይም የምትቀመጥበትን ነገር የነካ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


እነርሱንም የሚነካ ሁሉ ስለሚረክስ ልብሱን አጥቦ፥ ሰውነቱን ታጥቦ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


አልጋውን የሚነካም ሆነ፥


ወይም ሰውየው በተቀመጠበት በማንኛውም ነገር ላይ ሁሉ የሚቀመጥ ሰው ልብሱን አጥቦ፥ ሰውነቱንም ታጥቦ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሁን።


ፈሳሽ ያለበትን ሰው የሚነካ ሁሉ ልብሱን አጥቦ፥ ሰውነቱንም ታጥቦ፥ እስከ ማታ ድረስ የረከሰ ይሆናል።


ፈሳሽ ያለበት ሰው ንጹሕ በሆነ ሰው ላይ ምራቁን ቢተፋበት፥ ያ ሰው ልብሱን አጥቦ ሰውነቱንም ታጥቦ እስከ ማታ ድረስ የረከሰ ይሆናል።


እንዲሁም በልቡ የሚሳብ፥ የሚያረክስ ነገርን የሚነካ፥ ወይም ርኲሰቱ ምንም ዐይነት ቢሆን የረከሰውን ሰው የሚነካ፤


ማንኛውም ሰው እነዚህን ነገሮች ቢነካ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ገላውን በውሃ ካልታጠበ በቀር የተቀደሱትን ነገሮች አይብላ።


“አንድ ሰው ባለማወቅ ማናቸውንም ርኩስ ነገር ለምሳሌ የአውሬ፥ የቤት እንስሳ ወይም በደረቱ እየተሳበ የሚንቀሳቀስ ፍጥረት በድን ቢነካ፥ ያደረገውን ስሕተት ካወቀበት ጊዜ አንሥቶ በደል ይሆንበታል።


“አንድ ሰው ባለማወቅ ምንም ዐይነት ይሁን ከሰውነት የሚፈስ አንዳች ርኩስ ነገር ቢነካ፥ ያደረገውን ስሕተት ካወቀበት ጊዜ አንሥቶ በደል ይሆንበታል።


ንጹሕ የሆነውን ሥጋ ማንኛውም የረከሰ ነገር ቢነካው መቃጠል እንጂ መበላት የለበትም፤ “ንጹሕ የሆነ ሰው ይህን ንጹሕ የሆነውን ሥጋ ይብላ፤


ማንም ሰው ንጹሕ ያልሆነው ከሰው ወይም ከእንስሶች የሚወጣ ማንኛውንም ርኩስ ነገር ነክቶ ይህን የአንድነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ ያ ሰው ከእግዚአብሔር ሕዝብ ይለይ። ”


ሐጌም እንደገና “ሬሳ በመዳሰስ የረከሰ አንድ ሰው፥ ከነዚህ የምግብ ዐይነቶች አንዱን ቢነካ፥ ያ የተነካው ምግብ በዕርግጥ ይረክሳልን?” ሲል ጠየቃቸው። ካህናቱም “አዎ፥ ይረክሳል” ሲሉ መለሱለት።


ከዚህ በኋላ ልብሱን ይጠብ፤ ገላውንም በውሃ ይታጠብና ወደ ሰፈሩ ይመለስ፤ ነገር ግን ያልነጻ ሆኖ እስከ ማታ ድረስ ይቈይ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos