እነርሱም ለንጉሣዊው ቤተሰብና ለይሁዳ ሕዝብ የኃጢአት ስርየት፥ እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ መንጻት መሥዋዕት ሆነው ለእግዚአብሔር ይቀርቡ ዘንድ ሰባት ኰርማዎችን፥ ሰባት የበግ አውራዎችን፥ ሰባት የበግ ጠቦቶችንና ሰባት ፍየሎችን አመጡ፤ ንጉሡም የአሮን ዘሮች የሆኑትን ካህናት እንስሶቹን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ መሥዋዕት አድርገው እንዲያቀርቡ አዘዛቸው፤
ዘሌዋውያን 4:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ተቀብቶ የተሾመው ካህን ኃጢአት ሠርቶ ሕዝቡን እንደ በደለኛ የሚያስቈጥር ሆኖ ቢገኝ፥ ምንም ነውር የሌለበትን አንድ ወይፈን ያምጣ፤ ስለ ኃጢአቱም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ ያቅርበው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የተቀባውም ካህን በሕዝቡ ላይ በደል የሚያስከትል ኀጢአት ቢሠራ፣ ስለ ሠራው ኀጢአት እንከን የሌለበት አንድ ወይፈን ለእግዚአብሔር የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተቀባውም ካህን ኃጢአት ሠርቶ በሕዝቡ ላይ በደል ቢያመጣ፥ ስለ ሠራው ኃጢአቱ ነውር የሌለበት ወይፈን ለጌታ ለኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተቀባውም ሊቀ ካህናት በሕዝቡ ላይ በደል እንዲቈጠርባቸው ኀጢአት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኀጢአቱ ከመንጋው ነውር የሌለበትን ወይፈን ለእግዚአብሔር ለኀጢአት መሥዋዕት ያቀርበዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቀባውም ካህን በሕዝቡ ላይ በደል እንዲቈጠርባቸው ኃጢአት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኃጢአቱ ነውር የሌለበት ወይፈን ለእግዚአብሔር ለኃጢአት መሥዋዕት ያቀርበዋል። |
እነርሱም ለንጉሣዊው ቤተሰብና ለይሁዳ ሕዝብ የኃጢአት ስርየት፥ እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ መንጻት መሥዋዕት ሆነው ለእግዚአብሔር ይቀርቡ ዘንድ ሰባት ኰርማዎችን፥ ሰባት የበግ አውራዎችን፥ ሰባት የበግ ጠቦቶችንና ሰባት ፍየሎችን አመጡ፤ ንጉሡም የአሮን ዘሮች የሆኑትን ካህናት እንስሶቹን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ መሥዋዕት አድርገው እንዲያቀርቡ አዘዛቸው፤
ከዚያም ቀጥሎ እነዚያ ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ሁሉ ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውን መባ ሁሉ አመጡ፤ በዚህ ዐይነት በመላው እስራኤል ሕዝብ ስም ዐሥራ ሁለት ኰርማዎችን፥ ዘጠና ስድስት የበግ አውራዎችንና ሰባ ሰባት የበግ ጠቦቶችን አቀረቡ፤ እንዲሁም ስለ ኃጢአታቸው ስርየት ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎችን አቀረቡ፤ እነዚህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበሩ።
በመሠዊያው ላይ ካለው ደም ጥቂት፥ ከቅባቱም ዘይት ጥቂት ወስደህ በአሮንና በልብሱ ላይ በአሮን ልጆችና በልብሶቻቸው ላይ ርጨው፤ በዚህ ዐይነት እርሱና ልጆቹ ከነልብሶቻቸው ለእኔ የተለዩ ይሆናሉ።
አሮን በዓመት አንድ ጊዜ ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ከታረደው እንስሳ ደም ወስዶ በአራቱም ጒጦች ላይ በማድረግ መሠዊያው የሚነጻበትን ሥርዓት ይፈጽም፤ ይህም ሥርዓት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በየዓመቱ ይፈጸም፤ በዚህ ዐይነት ይህ መሠዊያ ለእግዚአብሔር በፍጹም የተቀደሰ ይሁን።”
በመግቢያው ክፍል በኩል በግራና በቀኝ ትይዩ ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ፤ በእነዚያም ጠረጴዛዎች ላይ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትና ለበደል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች ይታረድባቸው ነበር።
በፊቴ ቆመው እኔን ለሚያገልገሉ የሌዊ ነገድ ከሆነው ከሳዶቅ ዘር ለተወለዱ የኃጢአት ሥርየት መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡ ዘንድ ለእነርሱ አንድ ወይፈን ትሰጣቸዋለህ፤’ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።
ለአገልግሎት ወደ ውስጠኛው አደባባይ፥ ወደ መቅደሱ በሚገባበት ቀን ለኃጢአቱ መሥዋዕት ያቅርብ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
ይኸውም ከቀንድ ከብቱ መካከል አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ቢፈልግ ምንም ነውር የሌለበትን ኰርማ መርጦ ያምጣ፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት የሰመረ መሥዋዕት ይሆንለት ዘንድ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በኩል ያቅርበው።
ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት የሚችለውም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አንድ ወይፈን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕትም አንድ አውራ በግ ካቀረበ በኋላ መሆን አለበት።”
የተሠራው ኃጢአት እንደ ታወቀ ወዲያውኑ ማኅበሩ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት የሚሆን አንድ ወይፈን ያምጣ፤ እርሱንም ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ያቅርቡት፤
ስለ ሠራው ኃጢአት ለእግዚአብሔር የበደል መሥዋዕት ያምጣ፤ ይኸውም ከመንጋው የበግ ወይም የፍየል እንስት ይሆናል፤ ካህኑም ስለ ኃጢአቱ ያስተሰርይለታል።
በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ትውልዱ ከአሮን ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ለእግዚአብሔር ከቀረበው መባ ለእርሱ የተመደበለትን ፈንታ መብላት ይችላል፤ መባውን የሚነካ ሁሉ በቅድስናው ኀይል ይቀሠፋል።”
አሮንንም እንዲህ አለው፤ “ምንም ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና አንድ የበግ አውራ ወስደህ ወይፈኑን ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርብ መሥዋዕት፥ የበግ አውራውንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ለእግዚአብሔር አቅርብ።
ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን አንድ ተባዕት ፍየል፥ ምንም ነውር የሌለባቸውን የአንድ ዓመት ጥጃና የአንድ ዓመት የበግ ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያመጡ ንገራቸው።
ሙሴና አሮን በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው እንዲህ አሉ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ የሕይወት ሁሉ ምንጭ ነህ፤ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ በመላው ማኅበር ላይ ትቈጣለህን?”
ቀጥሎም አንድ ወይፈንና ለእህል ቊርባን የተመደበውን በዘይት የተለወሰ ዱቄት ይውሰዱ፤ አንተም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚቀርብ አንድ ወይፈን ውሰድ፤
ከሰው ባሕርይ ደካማነት የተነሣ ሕግ ሊያደርገው ያልቻለውን እግዚአብሔር አድርጎታል፤ የገዛ ልጁንም በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌነት በኃጢአት ምክንያት ልኮ በሥጋው ኃጢአትን በፍርድ አስወገደ።
እርሱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን አንዴ በማያዳግም ሁኔታ የራሱን ደም ይዞ ገባ እንጂ የፍየሎችንና የወይፈኖችን ደም ይዞ አልገባም፤ በዚህም ዐይነት የዘለዓለም ቤዛን አስገኘልን።